ብሪታንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ ሀገራት አበባ ያለ ግብር ወደ ሀገሯ እንዲገባ ፈቀደች

የብሪታንያ ንግድ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ብሪታንያ የአበባ ምርቶችን ወደ ሀገራቸው በሚያስገቡ ነጋዴዎች ላይ ጥላው የነበረውን ግብር አንስታለች፡፡

ሀገሪቱ ከዚህ በፊት የአበባ ምርቶች ወደ ብሪታንያ ሲገቡ 8 በመቶ ግብር መክፈል የነበረባቸው ሲሆን ከዛሬ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ማንሰቷን አስታውቃለች፡፡

የብሪታንያ ንግድ ኮሚሽነር ጆን ሀምፍሬይ እንዳሉት ወደ ብሪታንያ የሚገቡ የአበባ ምርቶች ከግብር ነጻ መሆናቸው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አበባ አምራች እና ነጋዴዎችን ተጠቃሚ ከማድረጉ ባለፈ በብሪታንያ የአበባ ምርት በቅ አቅርቦት እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ኬንያ፣ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል አበባ ላኪ ሀገራት ናቸው፡፡

እነዚህ አምስት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በቀጥታም ይሁን በሶተኛ ሀገር አድርገው ወደ ብሪታንያ ለሚያስገቡት የአበባ ምርት የገቢ ግብር አይከፍሉም ተብሏል፡፡

ብሪታንያ ወደ ሀገሯ ለሚገቡ የአበባ ምርቶች ይፋ ያደረገችው የግብር እፎይታ ለሁለት ዓመት እንደሚቆይ አስታውቃለች፡፡

ሀገሪቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ካላት ፍላጎት የተነሳ መሆኑንም አስታውቃለች፡፡

ኢትዮጵያ በ2023 ዓመት ብቻ 12 ነትብ 6 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ ያላቸው የአበባ ምርቶችን ወደ ብሪታንያ መላኳ ተገልጿል፡፡

ከአፍሪካ ሁለተኛ የአበባ አምራች የሆነችው ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ከሚመረተው ጠቅላላ የአበባ ምርት ውስጥ 23 በመቶውን ትሸፍናለች፡፡

ኬንያ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ አበባ አምራች ሀገር ስትሆን በዓለም ላይ ከሚመረተው ውስጥ የ6 በመቶ ድርሻ በመያዝ አራተኛዋ አበባ አምራች ሀገር እንደሆነች ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አበባ አምራቾች እና ላኪዎች ማህበር በበኩሉ የብሪታንያ መንግስት ያደረገው የግብር እፎይታ ጥሩ እና ስራቸውን የበለጠ እንዲሰሩ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች መካከል 30 በመቶውን ወደ አውሮፓ ሀገራት የምትልክ ሲሆን የአበባ ምርቶቿን በኔዘርላንድ በኩል አድርጋ ወደ ሌሎች ሀገራት በመላክ ላይ ትገኛለች፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *