የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከ4 ዓመታት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሊመለስ ነው

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 እግር ኳስ ውድድር የጨዋታ ፕሮግራም ባሳለፍነው ነሀሴ ከወጣ በኋላ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓም መጀመሩ ይታወሳል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታን ባለሜዳው አዳማ ከነማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል ተደርጎም ነበር፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ላለፉት አራት ዓመታት በአዳማ፣ ድሬዳዋ፣ሐዋሳ እና ባህርዳር ስታዲየሞች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የፕሪሚየር ሊግ እና የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎችን ወደ ክልል ከተሞች እንዲዞሩ የግድ ሆኖ ቆይቶም ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ እንደገለጸው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻዎቹ ሶስት ሳምንታት በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚደረግ ገልጿል።

የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መርሃ ግብርና የውድድር ሜዳዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም በስታዲየሞች ደረጃ ከ16ኛ እስከ 22ኛ ሳምንት በድሬዳዋ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን፤ ከ23ኛ እስከ 27ኛ ሳምንት ያለው በሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ይካሄዳል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል የመጨረሻዎቹ ሶስት ሳምንታት በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚደረግ ነው የተገለጸው፡፡

የሁለተኛ ዙር የውድድር መርሃ ግብሩም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ያሉበትን ጨዋታዎች እና የኢትዮጵያ ዋንጫ ቀጣይ ጨዋታዎችን ታሳቢ በማድረግ ይፋ መደረጉን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ መረጃ ያመለክታል።

የ2015 ቤቲኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉን በ64 ነጥብ አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ባህርዳር ከነማ ደግሞ በ60 እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን በ49 ነጥቦች የውድድር ዓመቱን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

የወራጅነት ደረጃዎች ላይ ደግሞ አርባምንጭ እግር ኳስ ክለብ በ34 ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ ክለብ በ18 እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ15 ነጥቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ ወርደዋል።

የኮኮብ ግብ አግቢነት ደረጃውን የቅዱስ ጊዮርጊሱ እስማኤል አጎሮ በ25 ጎሎች የውድድር ዓመቱ ኮኮብ ግብ አግቢ ሆኖ አጠናቋል።

እስካሁን በተደረጉት የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደረጃ መቻል በ33 ነጥብ ሊጎን ሲመራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ32 እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ በ28 ነጥብ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ያለውን እየመሩ ናቸው፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *