የ2023 አፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ በኮቲዲቯር አሸናፊነት ተጠናቀቀ

37ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር በውድድሩ አዘጋጅ ሀገር ኮቲዲቯር አሸናፊነት ተጠናቋል።

ጥር 3 ቀን ተጀምሮ የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ፍጻሜውን ያገኘው ይህ ውድድር ናይጀሪያ እና ኮቲዲቯር ለዋንጫ ተጫውተዋል።

ናይጀሪያ በመጀመሪያው አጋማሽ በአምበሏ ኢኮንግ ጎል ቀድማ ጎል ያስቆጠረች ቢሆንም ኬሲ እና ሀለር ኮቲዲቯርን የዋንጫ ባለቤት ያደረጉ ጎሎችን አስቆጥረዋል።

ይህን ውድድር ደቡብ አፍሪካ ሶስተኛ እንዲሁም ዲሞክራቲክ ኮንጎ አራተኛ ሆነው አጠናቀዋል።

በዚህ ውድድር ላይ የኮቲዲቯር አሰልጣኝ ኤምሬ ፋኤ ኮከብ አሰልጣኝ፣ ሲሞን አዲንጋራ ምርጥ ኮከብ ወጣት ተጫዋች

ናይጀሪያዊው ዊሊያም ኢኮንግ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች፣ የ34 ዓመቱ የኢኳቶሪያል ጊኒው ኤምሊያኖ ኑስ በአምስት ጎሎች ኮከብ ግብ አግቢ እንዲሁም ሮንውን ዊሊያምስ ኮከብ ግብ ጠባቂ በመሆን ተመርጠዋል።

ያለፉት ሶስት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች በአፍሪካዊያን አሰልጣኞች የተገኙ ሲሆን ዋንጫ ለማንሳት በሚል የውጭ ሀገራት ዜጎችን መቅጠር አዋጭ አለመሆኑን አሳይቷል ተብሏል።

የ2019 የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫን አልጀሪያ፣ የ2021 የአፍሪካ ዋንጫን ሴኔጋል በአሊዮ ሲሴ አሰልጣኝነት አግኝታለች።

በዘንድሮው በምዕራብ አፍሪካዊቷ አዘጋጅ ሀገር ኮቲዲቯር የተዘጋጀው የ2023 የአፍሪካ ዋንጫን በአሰልጣኝ ኤምሬ ፋኤ አማካኝነት ራሷ ያዘጋጀችውን ውድድር ራሷ አሸንፋለች።

ቀጣዩን የ2025 የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫን ከ37 ዓመታት በኋላ የሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ የምታዘጋጀው ይሆናል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *