የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው።

የደቡብ አሜሪካዋ ብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ አፍሪካ እንደሚመጡ ተገልጻል።

እንደ ብራዚል ዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ አዲስ አዲስ አበባ ይመጣሉ።

ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ በአዲስ አበባ ቆይታቸው በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉም ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ ከአዲስ አበባ በተጨማሪም በግብጽ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ተገልጿል።

ከአፍሪካ በመቀጠል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጥቁር ህዝቦች የሚኖሩባት ብራዚል ከአፍሪካ ጋር የሚያስተሳስራት ብዙ ታሪክ አላት።

ፕሬዝዳንቱ ዳ ሲልቫ ስለ ጉብኝታቸው እንዳሉት “ብራዚል ከአፍሪካ ጋር ያለባትን የታሪክ እዳ መክፈል ትፈልጋለች” ብለዋል።

ለሁለተኛ ጊዜ ወደ አፍሪካ የሚጓዙት ፕሬዝዳንት ሲልቫ ከዚህ በፊት በአንጎላ፣ ኬፕ ቩርዴ እንዲሁም በሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔ ጉብኝት አድርገው ነበር።

ብራዚል የቡድን 20 አባል ሀገር ስትሆን የፊታችን ህዳር ላይ የቡድኑን ዓመታዊ ጉባኤ እንደምታስተናግድ ይጠበቃል።

በብራዚል ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ጥቁር ብራዚሊያዊያን ሲሆኑ ይህም ከጠቅላላ ህዝቡ ውስጥ የ11 በመቶ ድርሻ አላቸው።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *