በአዲስ አበባ ያሉ የገበያ ቦታዎችን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት ሞል ኢን አዲስ የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ፡፡

ሜልፋን ቴክ በተሰኘ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ኩባንያ የተሰራው ሞል ኢን አዲስ መተግበሪያ በወጣት ኢትዮጵያዊያን የተሰራ ነው።

የመልፋን ቴክኖሎጂ ስራ አስኪያጅ አቶ መልካሙ ምትኩ በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት መተግበሪያው ፈጣን እና የእለት ተዕለት  ህይወታችንን በማቅለል ረገድ ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል።

መልፋን ቴክ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ ከአምስት አመታት በላይ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ከፌደራልና ከክልል አስተዳደሮች፣ ከግልና አንጋፋ ከሆኑ የአገሪቱ ተቋማት ጋር በርካታ ስራዎችን ሲሰራም ቆይቷል ብለዋል።

የተለያዩ የሶፍትዌር ስራዎችን፣ የሞባይልና የኮምፒውተር አፕልኬሽኖችን፣ የተቋማትን ሲስተም ማበልፀግን እና ለዲጂታል ኢትዮጵያ እቅድ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

መልፋን ቴክ ከ45 በላይ ለሚሆኑ ባለሙያዎች የስራ ዕድል ፈጥሮ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ድርጅቶች በደንበኝነት አፍርቶ፣ ከ14 በላይ መተግበሪያዎችንም አበልጽጓል።

የድርጅት ሀብት ማቀጃ/ERP/፣ የኢ-ኮሜርስ መተግበሪያ፣ የንብረት አስተዳደር ስርዓት፣ የትምህርት አስተዳደር ስርዓት፣ የሰው ኃይል አስተዳደር ስርዓት፣ የሆስፒታል አስተዳደር ስርዓት፣ የንብረት አያያዝ ስርዓት፣ በፍላጎት ላይ የተመሰረቱ ሶፍትዌሮችን እና ሌሎችም ስራዎችን ለደንበኞቹ ሰርቶ አስረክቧል።

ዛሬ ይፋ የተደረገው አዲሱ ሞል ኢን አዲስ ሶፍትዌር የማህበረሰባችንን ችግሮች በቴክኖሎጂ ለመፍታት እና ለድጅታል ኢትዮጵያ እቅድ መሳካት ያለንን ቁርጠኝነት ማሳያ ውጤት ነው።

መተግበሪያው ሂደቶችን ለማመቻቸት፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና ወደር የለሽ የተጠቃሚ ተሞክሮን ለማቅረብ የተነደፈ ነው ተብሏል።

የንግድ ባለሙያም ይሁኑ የፈጠራ ሰው ወይም የእለት ተእለት ተግባራቸውን ለማቃለል የሚፈልጉ ሰዎች የእኛ ሶፍትዌር ፍላጎታቸዉን ለማሟላት መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ሞል ኢን አዲስ መተግበሪያ ለማህበረሰቡ ካሉበት ቦታ ሆነዉ በቀላሉ የሚፈልጉትን ሰርቪስ ወይንም ምርት /ለምሳሌ ሲኒማ ቤት፣ ጸጉር ቤት፣ ባንክ ቤት ወዘተ/ ፣ የሚከራዩ ቢሮዎችን፣ የስራ ማስታወቂያዎችን እናም ሌሎች መረጃዎችን የት አካባቢ እና የትኛዉ ሞል ላይ እንደሚያገኝ በካርታ ጭምር እንዲያገኙ ያስችላል።

እንዲሁም ባሉበት ቦታም ሆነዉ ማመልከት የሚችሉበት፤ ለሞል ባለቤቶች ሞላቸዉን ተደራሽ ማድረግ፣ የሚከራዩ ቢሮዎችን ያለምንም ደላላ ማስተዋወቅ፣ የስራ ማስታወቂያዎችን መልቀቅ፣ ሞላቸዉን በዘመነ መንገድ ማስተዳደር፣ የተከራዮቻቸዉን ምርታቸዉን እና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ ያደርጋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *