ኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ላለችው የኢኮኖሚ ሪፎርም እና ችግር ላይ የሚገኘውን የፋይናንስ ሁኔታዋን ለመቅረፍ ያግዛት ዘንድ ከአለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር እየተነጋገረች መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
በሀገሪቱ የሚታየውን አመታዊ የበጀት ጉድለቷን ለሞሙላት ያግዛት ዘንድ በልዩ ሁኔታ ከአይኤም ኤፍ ብድር መጠየቋን ዘገባው አመላክቷል።
የመንግሥት ባለስለጣናት ባለፈው ሳምንት ከአለም አቀፍ ቦንድ ገዢዎች ጋር በነበራቸው ስብሰባ በቀጣዩ የፈረንጆች አመት 2024 መጀመሪያ ሶስት ወራት ከአይ ኤም ኤፍ ጋር የብድር ስምምነት ላይ እደርሳለን ብለው እንድደሚያምኑ ተናግረዋል።
ሀገሪቱ ያለት የገቢ ንግድ ማስኬጃ የውጭ ምንዛሬ መጠን ክምችት ዜሮ ነጥብ ሁለት በመቶ ብቻ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
ኢትዮጵያ የገጠማትን የበጀት ጉድለት ለመሙላት ከአይኤምኤፍ በተጨማሪ ከአለም ባንክ የሶስት ነጥብ አምስት ቢሊየን ዶላር የበጀት ድጎማ እንደምትፈልግም ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ከሁለቱ ተቋማት በተጨማሪ ከቻይና፣ አውሮፓ ህብረት እና አፍሪካ ልማት ባንክ ያለባት ብድር መጠን 28 ቢሊዮን ዶላር የውጭ እዳ እንዳለባት የገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በጦርነት ፣ ኮሮና ቫይረስ፣ ግጭቶች እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ችግሮች ምክንያት እየተፈተነ ይገኛል።
መንግሥት የውጭ ብድር ጫናውን ለመቋቋም አበዳሪ ተቋማት የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲያሻሽሉለት ጠይቋል።
ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ብድር ለኢትዮጵያ ያበደረችው ቻይና የመክፈያ ጊዜውን ለሁለት ዓመት ማራዘሟን አስታውቃለች።
ሌሎች አበዳሪ ሀገራት እና ተቋማት የብድር መክፈያ ጊዜ ለኢትዮጵያ እንዲያራዝሙ ውይይቶች እንደቀጠሉ ናቸው።
ኢትዮጵያ አይኤምኤፍ እና አለም ባንክ 10 ቢሊዮን ዶላር አዲስ ብድር እንዲሰጧት ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን ተቋማቱ ብድሩን ለመፍቀድ ሁኔታዎችን በመገምገም ላይ እንደሆኑ አስታውቀዋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሁለት ዓመታት በተካሄደውና በሌሎች የተወሰኑ አካባቢዎች በነበረው ጦርነት፣ ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ማድረሱን ገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ይህ ጦርነት ለዓመታት በብድር እና በህዝብ ገንዘብ የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን እንዲወድም ያደረገ ሲሆን በአጠቃላይ የ28 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ በሀገር ላይ እንዳደረሰ ተገልጿል።