አይቴል ሞባይል አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና ላለፉት አመታት ዘመናዊ እና ጥራት ያላቻውን የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን በሚንቀሳቀስባቸው ለተለያዩ የአለም ገበያዎች ለተጠቃሚዎች በማቅረብ የሚታወቀው አይቲል ሲጠቀምብት የነበረው የምርት አርማ እና መለዮ በአዲስ መልክ መቀየሩን አስታወቀ።

በትራንሽን ማኑፋክችሪንግ ስር የሚንቀሳቀሰው አይቴል ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ሲሰራ የቆየውን አገልግሎት በአዲስ እና እጅጉኑ በተሻሻለ መለኩ ለማከናወን የሚያስችለው አዲስ የቢዝነስ እስትራቴጂ አንዱ አካል የሆነውን የምርት አርማ እና መለዮ የመቀየር ስራ በመጪው ጊዚ ለመተግበር የወጠናቸውን ልዩ ልዩ ስራዎች መሰረት እንደሚሆንም አሳውቆል። 

አይቴል ይፋ ካደረገው አዲሱ አርማ እና መለዮ ለውጥ በተጨማሪ ኩባንያው በሚሰራባቸው እና ምርቱን ለገበያ በሚያቀርብባችው ሀገራት ውስጥ ሲተገብር የነበራቸውን የማህበረሰብ ተኮር ስራዎች በማስቀጠል በሎም ትርጉም ያለው ተጽእኖ ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ ተጠቃሚዎቹን ያማክሉ የቴክኖሎጂ ፍላጎቶችን የማሟላት እና የማሳደግ ብሎም የለት ተለት ኑሮን ያሚያሻሽሉ የኤሌክትሮኒክስ መርቶቹን ለተጠቃሚዎቹ በተሻለ መልኩ ለማቅረብ ይሚረዱ ስትራቴጂዎችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ላሉ ህገራት ውስጥ የሚተገብር ይሆናል።

ከ16 ዓመታት በፊት የተመሰረተው አይቴል የተጠቃሚዎችን ልዩ ፍላጎቶች በመረዳት እና በየጊዜው የሚሻሻሉ የቴክኖሎጂ እድገቶችን በመጠቀም “የብልህ ህይወት”(Smart Life) በሚል መርህ የጀመረውን የቴክኖሎጂ ምርቶቹን ለተጠቃሚዎቹ የማቅረብ አላማ በአሁኑም ውቅት በቁርጠኝነት አጸንቶ እያስቀጠለ ይገኛል።

ከኤሌክትሮኒክስ ብራንድ ወደ ሁለንተናዊ “ብልህ ህይወት” (Smart Life) ብራንድ በማሳደግ፣ ኢይቴል የተለያዩ የግልጋሎት ፍላጎቶችን የሚያሟሉ የብራንድ ስነ-ምህዳሮች እንዲፈጠሩ አድርጓል።

የአይቴል ኢትዮጵያ ብራንድ ስራ አስኪያጅ ሚስተር ኤሞን ጃ ስለ አርማ እና መልዮ ለውጡ አስመልክተው ሲናገሩ ”በአይቴል ውስጥ የምናደርጋቸው ማናችውም አይነት ለውጦች ሁሌም የተጠቃሚዎቻችንን ፍላጎት ለማሟላት በሎም የዘመነ የእለት ተለት እቅስቃሴን ለማገዝ ሁነኛ ግብዓት የሚሆኑ የቲክኖሎጂ ውጤቶችን ለማቅረብ የሚተገበሩ ሲሆን ሁሉም በአይቲል ውስጥ ይሚደረጉ የለውጥ ውሳኔዎቻችን ከመጀመሪያውም የተነሳንበትን “የተሻለ ህይውት” (Better Life) ማጎናዕፍ የሚለውን አላማ መሰረት ያደረገ ነው።

የአሁንም የ አዲሱ ስትራቴጂ አካል የሆነው የመልዮ እና አርማ ለውጥ አንዱ አካል በማድረግ የማህበረስብ ተኮር ስራዎቻችንን ክምንጊዜውም በላይ በስፊው የምንናስቀጥል ይሆናል።”

ኢይቴል ብራንድ ስማርት ስልኮችን የተለያዩ የኤለክትሮኒክስ ፍላጎቶችን የሚያሞሉ የቤት ውስጥ እና የቢሮ መገልገያዎችን ያካተቱ ምርቶቹን በየጊዜው በፍጥነት እያዘመነ በማቅረብ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም ብራንዱ በሚንቀሳቀስባቸው ሀገራት ውስጥ ተጠቃሚዎቹን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የህይወት ይኖራቸው ዘንድ የሚተገብረው አላማ አካል እንደሆነ አስታውቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *