አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እንደሚሰጋት ገለጸች

የአሜሪካ የታችኛው ምክር ቤት ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ጉዳዮች ንኡስ ኮሚቴ፣  ‘”በኢትዮጵያ ተስፋ ወይንስ ስጋት፣ የአሜሪካ ፖሊሲ ሁኔታ’’ ላይ ትላንት ምሸት ምስክርነት ሰምቷል፡፡

የኮሚቴው አባላት ለአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር፣ ስለ ባህር በር በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስለተነሳው ጥያቄ የአሜሪካን አቋም ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “የወደብ ጉዳይ ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው” ብለው መናገራቸው በቀጠናው ካሉ አገራት አልፎ ለአሜሪካ ስጋት እንደሆነ ማይክ ሐመር ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የባህር በር ፍላጎት በኃይል ተፈጻሚ እንደማይሆን በይፋ እንዲሁም በግል ማረጋገጫ እንደሰጧቸው አመልክተዋል።

ጥያቄው በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ስጋት እንደፈጠረ የጠቆሙት ማይክ ሐመር፣ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ የሚቀጠል ከሆነ አሜሪካ እንደማትቃወም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያም ትሁን የቀጠናው አገራት ተጨማሪ ጦርነት ውስጥ መግባት እንደሌለባቸውም ልዩ መልዕክተኛው ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆኑት ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ ያሉ ጎረቤት አገራት የኢትዮጵያን ጥያቄ በስጋትነት እንደተመለከቱት አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ያነሳችው ወደ ቀይ ባህር የመቅረብና የባህር በር ጥያቄ ከጎረቤት አገራት ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ ብቻ እንዲሳካ የተለያዩ ወገኖችን እያሳሰቡ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንደ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሌኮም መሰል መሰረተ ልማቶች ላይ የጎረቤት ሀገራትን በማሳተፍ የወደብ ተጠቃሚ እንድትሆን ጥያቄ ማቅረባቸው አይዘነጋም።

ሶስቱም የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን ኤርትራ ጉዳዩን ብአትኩረት እየተከታተለችው እንደሆነ ገልጻለች።

ኢትዮጵያ 90 በመቶ የወጪ እና ገቢ ንግዷን የምታከናውነው በጅቡቲ ወደብ በኩል ሲሆን በዓመት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለወደብ ኪራይ በማውጣት ላይ ትገኛለች።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *