ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ግጭት ውስጥ መግባቷን አመነች

የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥታል።

የሚንስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በተለያዩ የዲፕሎማሲ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቃል አቀባዩ ማብራሪያ ከሰጡባቸው ጉዳዮች መካከል ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ልማት ባንክ መክፈል ያለባትን ብድር ከመክፈል ጋር በተያያዘ አለመግባባት ተፈጥሯል የሚለው ጉዳይ ነው።

አለመግባባቱ በኢትዮጵያ ገንዘብ ሚንስቴር እና በአዲስ አበባ ካለው የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ቢሮ ጋር መካከል ነው የተባለ ሲሆን በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያትም ባንኩ ቢሮውን ዘግቶ ሆዷል የሚል ነበር።

በሁለቱ አካላት መካከል የተፈጠረው ግጭት ምንድን ነው? ባንኩስ የኢትዮጵያ ቢሮውን ዘግቶ ወጥቷል? በሚል ለአምባሳደር መለስ ዓለም ጥያቄ ከጋዜጠኞች ቀርቦላቸው ነበር።

አምባሳደር መለስ በምላሻቸውም “ከአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ቢሮ ጋር የተፈጠረው ክስተት ባንኩ ቢሮውን እንዲዘጋ አላደረገውም፣ የሁለቱ ግንኙነትም አልተቋረጠም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

የአፍሪካ ባንክ በበኩሉ በኢትዮጵያ ያሉ ሁለት የባንኩ ሰራተኞች በኢትዮጵያ መንግሥት እንደታሰሩ እና እንግልት እንደደረሰባቸው አስታውቋል።

ባንኩ አክሎም በሁለት ሰራተኞቹ ላይ የደረሰውን እስር እንግልት እንደማይቀበል ገልጾ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት በማድረግ ላይ መሆኑንም አስታውቋል።

ሌላኛው ቃል አቀባዩ ማብራሪያ የሰጡበት ጉዳይ ዓለም አቀፉ የጥቁር ህዝቦች ማዕከል ዋና መቀመጫውን በአዲስ አበባ ማድረጉን ነው።

ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተገዛች ሀገር መሆኗ፣ የጸረ ቅኝ ግዛት ትግሎችን ማገዟ፣ በርካታ የጥቁር ህዝቦች ድምጽ የሚሰሙባቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲመሰረቱ ድጋፍ ማድረጓ እና ሌሎችም ጉዳዮች ማዕከሉ ዋና ከተማውን አዲስ አበባ እንዲያደርግ ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑም ተገልጿል።

ማዕከሉ ለዋና ከተማነት አዲስ አበባን እንዲመርጥ ዲፕሎማቶች፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች እና ዲያስፖራዎች የማግባባት ስራ መስራታቸውንም አምባሳደር መለስ ተናግረዋል።

የዓለም አቀፍ ጥቁር ህዝቦች ማዕከል ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መሆን የኢትዮጵያን ተሰሚነት ከፍ ያደርጋል ያሉት አምባሳደር መለስ የጎብኚዎችን ቁጥር በማሳደግም ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙም ከፍተኛ እንደሚሆንም ጠቅሰዋል።

የዓለም ታዳጊ ሀገራት ትብብር ወይም ግሎባል ሳውዝ ኮኦፕሬሽን የተሰኘው ተቋም ካሳለፍነው ሕዳር ወር ጀምሮ አዲስ አበባ ዋና መቀመጫ ከተማው አድርጎ መምረጡ ይታወሳል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *