አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ዋልያዎቹን በአሰልጣኝነት ተረከቡ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሐየራዊ ቡድን አሰልጣን የነበሩት ገብረመድህን ሀይሌ በድጋሚ ዋልያዎቹን እንዲያሰለጥኑ ተመርጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው የኢትዮጵያ መድን እግር ኳ ክለብን በማሰልጠን ላይ የነበሩት አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ በአንድ ዓመት ውል ብሔራዊ ቡድኑን እንዲያሰለጥኑ ተመርጠዋል፡፡

አሰልጣኙ የብሔራዊ ቡድን ስራቸውን ከኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ክለብ ጋር ደርበው እንዲያካሂዱ ከፌዴሬሽኑ ጋር እንደተስማሙም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ የሚያደርጋቸውን ሁለት ቀጣይ የሜዳው ጨዋታዎችን ወደ ሞሮኮ ተጉዘው ያካሂዳሉም ተብሏል።

የመጀመርያው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከሴራሊዮን ኅዳር 5 እንዲሁም ሁለተኛው ጨዋታ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ኅዳር 11 የሚደረግ ሲሆን ሁለቱም ጨዋታዎች በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ይደረጋሉ፡፡

ብሄራዊ ቡድኑን በኢንተርናሽናል ውድድር ተፎካካሪ ማድረግ የሚጠብቅባቸው አሰልጣኝ ገብረመድህን ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ ጨዋታ የተመረጡ ተጨዋቾች ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

አሰልጣኝ ገብረመድህን ከፌዴሬሽኑ ጋር የአሰልጣኝነት ስምምነትን ከፈረሙ በኋላ እንዳሉት ” የማያሳፍር ውጤት በሁለት ጨዋታ እንዳይመዘገብ እጥራለሁ፣  ሊያግዙኝ የሚችሉት ረዳቶችንም እመርጣለሁ” ብለዋል፡፡

እስከ ቀጣዩ ሰኔ ወር ድረስ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ጋር ውል ያላቸው አሰልጣኝ ገብረመድህን በወር የተጣራ 250 ሺህ ብር ይከፈላቸዋልም ተብሏል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *