ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ቻይና አመሩ

የቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ዓመታዊ ጉባኤ ከሁለት ቀናት በኋላ በቤጂንግ ይካሄዳል፡፡

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን መሪዎች በዚህ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ቤጂንግ በማምራት ላይ ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዚሁ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ቻይና ማምራታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ቻይና ለኢትዮጵያ ብድር ከሚሰጡ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ስትሆን በተለይም ለኤርፖርት ማስፋፊያ፣ ለመንገድ እና ለደረቅ ወደብ ልማት ግንባታዎች በቻይና ብድር ተገንብተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በጦርነት እና በኮሮና ቫይረስ መጎዳቱን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት የብድር ጫና ውስጥ በመግባቱ የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምለት በመጠየቅ ላይ ነው፡፡

ቻይና የኢትዮጵያን የብድር መክፈያ ጊዜ በአንድ ዓመት ማራዘሟ የተገለጸ ሲሆን ከዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍ ጋር ውይይቶች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ 28 ቢሊዮን ዶላር የውጭ እዳ እንዳለባት ብሔራዊ ባንክ ያስታወቀ ሲሆን ከፍተኛ የብድር ጫና ካለባቸው ሀገራት መካከልም አንዷ ነች፡፡

በትግራይ አማራ እና አፋር ክልሎች በነበረው ጦርነት ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኪሳራ በአገር ላይ ማድረሱን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡


የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እንዳሉት በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተካሄደው ጦርነት ያጋጠመው አጠቃላይ የኢኮኖሚ ኪሳራ 28 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ተገልጿል።

ኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ተጨማሪ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት ድርድር በማድረግ ላይ ሲሆኑ የዓለም ባንክ ያስቀመጣቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ላይ ትገኛለች፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *