የአሜሪካ የልማት ተራድዖ ድርጅት በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የምግብ እርዳታ ዳግም አስጀመረ

እርዳታው የተጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት ከእርዳታው ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ስምምነት እንደማይኖረው ከተስማማ በኋላ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የምግብ እርዳታ ለስደተኞች ብቻ መልሶ ለማስጀመር መወሰኑን አስታውቋል።

ድርጅቱ የእርዳታ እህል አቅርቦቱን የሚጀምረው በኢትዮጵያ ለሚገኙ ለኹሉም የእርዳታ ፈላጊዎች ሳይሆን፤ በአገሪቱ ተጠልለው ለሚገኙ የጎረቤት አገራት ስደተኞች ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የረድኤት ድርጅቱ የኢትዮጵያ መንግሥት እና አጋሮቹ የስደተኞች የምግብ እርዳታ አቅርቦት መዋቅር ላይ ለውጦችን በማድረጋቸው እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱን የገለጸ ሲሆን፤ “የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሪቱ ለሚገኙ ስደተኞች የምግብ እርዳታን በማጓጓዝ፣ በማከማቸት እና በማከፋፈል ዙሪያ ምንም አይነት ተሳትፎ እንደማይኖረው ስምምነት ላይ በመደረሱ የእርዳታ እህል አቅርቦቱን ለመስጀመር መወሰኑን ተገልጿል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ ለሚገኙ አንድ ሚሊየን ለሚሆኑ ከሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ሌሎች አከባቢዎች ለመጡ ስደተኞች የሚውል የእርዳታ እህል አቅርቦት እና ክምችት እንደሚኖር አመላክቷል።

ዩኤስኤአይዲ በመግለጫው፣ “የምግብ እርዳታ በሚያስፈልግባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ድጋፉ ለታለመላቸው ተጠቃሚዎች እንደሚደርስ ማረጋገጫ እስክናገኝ ድረስ ተቋርጦ ይቆያል” ብሏል፡፡

የምግብ እርዳታው ቢቋረጥም የጤና እና የአልሚ ምግቦች እርዳታዎችን ጨምሮ ሌሎች የአሜሪካ መንግሥት የእርዳታ አቅርቦቶች ግን እንደሚቀጥሉ ገልጿል፡፡

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ከሚያቀርቡ ድርጅቶች መካከል ዋነኛ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን የእርዳታ አቅርቦት በመጀመሪያ ያቆረጠው በትግራይ ክልል ነበር፡፡

በማስከተልም ከወራት በፊት “በአገሪቱ የሚቀርበው የምግብ እርዳታ በከፍተኛ መጠን እና በተቀናጀ ኹኔታ ከታቀደለት አላማ ውጪ ጥቅም ላይ ውለዋል” በማለት፤ በመላው አገሪቱ የሚያደርገውን የምግብ እርዳታ እንደተቋረጠ ነው፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *