የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወጣት አፍሪካውያን መሪዎች ሽልማትን አሸነፉ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ በChoiseul100Africa በአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ ትልቅ ሚና ከሚጫወቱ 100 ወጣት አፍሪካዊ መሪዎች መካከል በአንደኛ ደረጃ ተመረጡ።

“Choiseul 100 አፍሪካ” ልዩ የሆነ በሿዘል ኢንስቲትዩት የሚደረግ ጥናት ሲሆን አፍሪካን ወደ ከፍተኛ የኢኮኖሚ፣ የማህበረሰብ እና የባህል እድገት ደረጃ የማድረስ አላማ ያነገበና እድሜያቸው 40 እና ከዚያ በታች የሆኑትን 200 ወጣት የአፍሪካ መሪዎችን በመለየት እውቅና የሚሰጥ በፈረንሳይ የሚገኝ ተቋም ነው።

ኩባንያው ሽልማቱን አስመልክቶ ባሰራጨው መግለጫ “…የሞባይል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን፣ የዲጂታል እና የፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ  ላከናወኗቸውናእና እያከናወንን ላለናቸው ስራዎችና ስለጥረታችን  የተሰጠ አበረታች እውቅና መሆኑን በመገንዘብ ታላቅ ኩራት ይሰማናል” ብሏል።

ፍሬህይወት ታምሩ ከ2018 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ንብረት የሆነው ኢትዮ ቴሌኮምን በስራ አስፈጻሚነት በመምራት ላይ ናቸው።

ድርጅቱ የተሻለ ትርፋማ እንዲሆን፣ ድጅታል አገልግሎቶች እንዲስፋፉ እና የቴሌኮም አገልግሎቶች እንዲስፋፉ የስራ አስፈጻሚዋ ጥረት ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *