የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ በላቲቪያ ሪያ በመደረግ ላይ ሲሆን የወንዶች እና የሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ፍጻሜውን አግኝቷል።
በወንዶች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት ውድድሩን አጠናቀዋል።
አትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት 12:59 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ደግሞ በ13:02 በመግባት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።
ኢትዮጵያዊው አትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ የወንዶች 5ኪ.ሜ ውድድርን ማሸነፍ የቻለ የመጀመሪያው አትሌት ሆኗል።
በሴቶች ተመሳሳይ ርቀት ውድድር ኬንያዊያኑ አትሌት ቺቤት አንደኛ እንዲሁም ናሬንጉሩክ ሁለተኛ ሆና ስታጠናቅቅ ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች እጅጋየሁ ታዬ እና መዲና ኢሳ ደግሞ ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በሌላ የ1 ማይል ርቀት ውድድር ደግሞ አትሌት ድርቤ ወልተጂ ኬንያዊቷን የ 1500ሜ የአለም ሪከርድ ባለቤት ፌዝ ኪፕዬጎን በመርታት ለሀገሯ ወርቅ አምጥታለች።
ድርቤ ወልተጂ ከማሸነፍ ባለፈም የአለም የአንድ ማይል ሪከርድን 4:21.00 በመግባት በመስበር ልታሸንፍ ችላለች።
በርቀቱ የተካፈለችው ሌላኛዋ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ለሀገራችን ሁለተኛውን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችላለች።
ድርቤ ወልተጂ በቡዳፔሽት የዓለም ሻምፒዮና በ 1500ሜ በፌዝ ኪፕዬጎን ተቀድማ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ ማምጣቷ የሚታወስ ነው።
ኬንያዊቷ ስኬታማ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን በ2023 የውድድር ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ሽንፈትን አስተናግዳለች።