ስድስት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በአበረታች መድሀኒት ምክንያት ለዓመታት ከውድድሮች ታገዱ

የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በተጠረጠሩ አትሌቶች ላይ ጊዜያዊ እገዳ በመጣል ጉዳዩን ሲያጣራ መቆየቱን አስታውቋል።

እገዳ የተላለፈባቸው አይሌቶች አትሌት ሹሜ  ጣፋ ደስታ እና  አትሌት መንግስቱ በቀለ ተዴቻ  የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግ በመጠቀም የህግ ጥሰት የፈፀሙ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብላል።

በዚህም መሠረት የረጅም ርቀት ሯጭ የሆነዉ አትሌት  ሹሜ ጣፋ ደስታ 5-methylhexan-2-amine የተባለውን የተከለከለ ንጥረ-ነገር ተጠቅሞ በፈፀመው  የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት በውድድሩ ያስመዘገበው ውጤት እንዲሰረዝ እና  እ.ኤ.አ ከግንቦት 25/2023  ጀምሮ ለአራት (4) አመታት በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ  የቅጣት ውሳኔ እንደተላለፈበት ተገልጿል።

በተመሳሳይ መልኩ አትሌት መንግስቱ በቀለ ተዴቻ ቻይና አገር ውስጥ በነበረው ውድድር ላይ Erythropoietin (EPO) የተባለዉን የተከለከለ አበረታች ቅመም ተጠቅሞ በመገኘቱ የፀረ- አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት መፈፀሙ የተረጋገጠ ሲሆን በውድድሩ ያስመዘገበው ውጤት እንዲሰረዝ እና ከመጋቢት 08 /2023 ጀምሮ ለአንድ  ዓመት ከስድስት ወር (1 ዓመት ከ6 ወር) በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጥሎበታል፡፡

እንዲሁም አትሌት ፋንቱ ኢቲቻ ጅማ Erythropoietin (EPO) የተባለውን የተከለከለ አበረታች ቅመም ለሁለተኛ ጊዜ ተጠቅማ በመገኘቷ ለአምስት (5) አመታት በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ እንዳትሳተፍ እና በውድድሩ ያስመዘገበችው  ውጤት እንዲሰረዝ ቅጣት ተጥሎባታል።

በሌላም በኩል አትሌት ኢብሴ አየለ፣ አትሌት ብርቱካን ዋቄ፣ መንግስቱ ንጋቱ  እና አትሌት ተሾመ ጌታቸው በተለያየ ጊዜ የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን በመጠቀም በፈፀሟቸው የህግ ጥሰቶች ምክንያት የቅጣት ውሳኔዎች ተላልፎባቸዋል ተብላል።

የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን  የስፖርት አበረታች ቅመሞችን በመጠቀምም ይሁን በተለያዩ መልኩ የፀረ-ዶፒንግ የህግ ጥሰት በሚፈፅሙ አትሌቶችና ከጀርባ ሆነው በሚተባበሩ ሌሎችም ግለሰቦች ላይ እርምጃ ሙውሰዴን እቀጥላለሁ ሲል አስታውቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *