የፌዴራል ቤቶች ኮርፓሬሽን ለዲያስፓራ ኢትዮጵያውያን ቤት መሸጥ ሊጀምር መሆኑን ገለጸ

ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ ሀይል እና እቅድ ወደ ስራ መግባቱን የገለጸው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሃገር ውስጥ ካለው ነዋሪ ባሻገር በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን ኘሮጀክት ለመጀመር ዝግጅት እያደረኩ ነው ብሏል።

ስለ ኘሮጀክቱ እና ስለተቋሙ ገለፃ ለማድረግም በኮርፓሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ረሻድ ከማል የተመራ ልዑክ ወደ ብሪታንያ በማምራት በዚያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የማህበረሰብ አመራሮች ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውንን ተጠቃሚ ለማድረግ በአዲስ መልክ ያቀደውን የቤት ልማት ፕሮጀክት ስኬታማ እንዲሆን ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ተጨማሪ ሀሳበችንና ተሞክሮዎችን መሰብሰቡ ተገልጻል።

ከዚሁ ጎን ለጎን በዋና ስራ አስፈፃሚው የሚመራው የልዑካን ቡድኑ በለንደንና አካባቢው በሚገኙ ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላ የተካሄዱ የቤት ልማት ፕሮጀክቶችንም ጎብኝተዋል፡፡

ነዋሪነታቸው ለንደንና አካባቢው ከሚገኙ በቤት ልማት ፕሮጀክቶች ዙሪያ የካበተ ልምድ ካላቸው ባለሀብቶችና መሀንዲሶች ጋርም ውይይት መካሄዱ ታውቋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *