አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ አራዘመች

አሜሪካ ከሁለት ዓመት በፊት የተቀሰቃሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የአሜሪካንን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ይጎዳል በሚል ነበር ጦርነቱ እንዲቆም ጫና ስታደርግ የቆየችው፡፡

ይህ ጦርነት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ምስራቅ አፍሪካን ይጎዳል የምትለው አሜሪካ ጦርነቱ እንዲቆም የተለያዩ ጫናዎችን ያደረገች ሲሆን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል በሚል የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች፡፡

በዋሸንግተን ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል በኢትዮጵያ ላይ ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ማዕቀብ የሚባል ሲሆን በፈረንጆቹ መስከረም 2021 ላይ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ማዕቀብ ተጥሏል፡፡

ይህ ማዕቀብ ከአንድ ሳምንት በኋላ የሚጠናቀቅ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማዕቀቡ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲራዘም መፈረማቸውን አስታውቀዋል፡፡

አሜሪካ ማዕቀቡን ለአንድ ዓመት ያራዘመችው በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሁንም ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለምስራቅ አፍሪካ እና ለአሜሪካ የውጭ ጉዳዮች ፖሊሲ ስጋት ነው በሚል ነው፡፡

አሜሪካ ኢትዮጵያን ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጻሚ ሀገርነት ዝርዝር ውስጥ ሰረዘች
የዓለማችን ባለግዙፍ ኢኮኖሚ የሖነችው አሜሪካ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚጎዳ ክስተት በየትኛውም ሀገር ሲከሰት ጥቅሟን ለማስከበር ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ ትግበራ የተሰኘ ፖሊሲ ያላት ሲሆን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት በቀጥታ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ ይፈቅዳል፡፡

ኢትዮጵያ እስካሁን በአሜሪካ አዲስ እርምጃ ዙሪያ ምላሽ ያልሰጠች ሲሆን የአግዋ እገዳ እንዲነሳ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ መሆኗን ከዚህ በፊት በተሰጡ መግለጫዎች ላይ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ በየዓመቱ ምርቶቿን ከቀረጽ ነጻ በሆነ መንገድ ወደ አሜሪካ ከተሞች በመላክ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ በማግኘት ላይ ነበረች።

የአሜሪካ የኢኮኖሚ ማዕቀብ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ገብተው በማምረት እና ምርቶቻቸውን ለዓለም ገበያዎች በመሸጥ ላይ የነበሩ ኩባንያዎችን ጎድቷል።

የአሜሪካን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ተከትሎ በርካታ ኩባንያዎች ኢትዮጵያን ለቀው በመሰደድ ላይ ናቸው

እገዳው ይነሳል በሚል በኢትዮጵያ የቆዩ ኩባንያዎች እስካሁን ሲጠባበቁ የቆዩ ሲሆን ፕሬዝዳንት ባይደን ያራዘሙት ማዕቀብ ተጨማሪ ኩባንያዎች እንዲሰደዱ ሊያደርግ እንደሚችል ተሰግቷል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *