እስራኤል ሁከት የፈጠሩ ኤርትራዊያንን ለማባረር ወሰነች

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በቴላቪቭ በሃይለኛ ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ኤርትራውያን በአስቸኳይ እንዲባረሩ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

የሀገሪቱን አፍሪካውያን ስደተኞች በሙሉ ለማስወገድ እቅድ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል።

ይህንን አስተያየት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት በደቡባዊ ቴል አቪቭ በኤርትራ ተቀናቃኝ ቡድኖች መካከል በነበረ ደም አፋሳሽ ግጭት በርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት ከደረሰ  ከአንድ ቀን በኋላ ነበር።

ኔታንያሁ የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ በትላንትናው እለት በተጠራው ልዩ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ “በሁከት ፈጣሪዎች ላይ ከባድ እርምጃዎችን እንፈልጋለን ፣ የተሳተፉትን ወዲያውኑ ወደ መጡበት መመለስ እንፈልጋለን” ብለዋል ።

ሚኒስትሮቹ “ሌሎች ህገወጥ ሰርጎ ገቦችን ለማስወገድ” እቅድ እንዲያቀርቡላቸው የጠየቁ ሲሆን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ስደተኞቹን ለቀው እንዲወጡ ለማስገደድ የታቀዱ አንዳንድ እርምጃዎችን መተላለፉን በንግግራቸው አስታውቀዋል።

በአለም አቀፍ ህግ እስራኤል ስደተኞችን በግዳጅ ህይወታቸው ወይም ነጻነታቸው አደጋ ላይ ወደ ሚወድቅበት ሀገር መላክ አትችልም።

ወደ ቆጵሮስ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ከማድረጋቸው በፊት ኔታንያሁ እንዳሉት የሚኒስትሮች ቡድኑ በቅዳሜው ሁከት ውስጥ የተሳተፉ 1,000 ኤርትራዊያንን ከሀገር ለማስወጣት እየፈለገ ይገኛል።

በእስራኤል 25,000 አፍሪካውያን ስደተኞች በእስራኤል የሚኖሩ ሲሆን በተለይም ከሱዳን እና ከኤርትራ የመጡ ዜጎች ተገን ጠያቂ ናቸው

እስራኤል ግን አብዛኛዎቹን ስደተኞች እንደ ኢኮኖሚያዊ ስደተኛ የተቀበለች በመሆኑ እነሱን የመጠበቅ ህጋዊ ግዴታ እንደሌለባት ትናግራለች።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *