በአማራ ክልል ከ50 በላይ ወረዳዎች ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ባለዉ ጦርነት ምክንያት ክልሉ ከመንግሥት መዋቅር ውጪ ናቸው የተባሉ ወረዳዎች ይፋ ሆነዋል።

መንግስት ከቁጥጥር ውጪ የሆኑ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳድር የባንክ ሂሳቦችን እንዳይንቀሳቀሱ እገዳ ጥሏል።

ከሰሜን ሸዋ ወረዳዎች ውስጥ ሚዳ ወረሞ፣ መርሃቤቴ፣ አለም ከተማ ፣እነዋሪ፣ መንዝ ቀያ፣ መንዝ ላሎ፣ መንዝ፣ ማማ፣ መንዝ ሞላሌ ከተማ አስተዳድር፣ መንዝ ጌራ፣ ሲያደብር እና ዋዩ፣ እንሳሮ ፣ሞረትና ጅሩ ወረዳዎች ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ናቸው ተብሏል።

ከሰሜን ወሎ ወረዳዎች ደግሞ ግዳን ወረዳ ፣እስታይሽ፣ ቡግና እና ሙጃ ወረዳዎች እንዲሁም ከደቡብ ወሎ ደፍሞ ወግዲ ወረዳ፣ ከለላ፣ መካነሰላም ፣ቦረና ፣ አማራ ሳይንት እና ዋድላ ደላንታ ወረዳዎች ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ናቸው የተባለ ሲሆን የመንግስት ተቋማት የባንክ ሂሳብ እንዳይንቀሳቀሱ እገዳ ተጥሎባቸዋል።

ከደቡብ ጎንደር ወረዳዎች ደግሞ ደብረታቦር ከተማን ጨምሮ በዚህ ዞን ስር ያሉ ሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ሁሉም የጎጃም ዞኖች የባንክ ሂሳባቸው ላይ እግድ መጣሉ ተገልጿል።

ከማዕከላዊ ጎንደር ወረዳዎች ደግሞ ምዕራብ ደንብያ ወረዳ፣ ጣቁሳ፣ አለፋ፣ ምስራቅ ደንብያ፣ ሻውራ፣ ቆላድባ ወረዳዎች እንዲሁም ከምዕራብ ጎንደር ወረዳዎች ደግሞ ቋራ ወረዳ ከመንግስት ቁጥጥር ስር አይደሉም ተብሏል።

ከሰሜን ጎንደር ወረዳዎች ደግሞ ጃናሞራ ወረዳዎች ከመንግሥት መዋቅር ውጪ ናቸው የተባለ ሲሆን የወረዳዎቹ ቼኮች ተዘርፈዋል በሚል የገንዘብ ዝውውር እንዳይኖር የክልሉ ገንዘብ ቢሮ እንዳገዳቸው ተገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *