የጸጥታ ሀይሎች በአማራ ክልል ሰላማዊ ዜጎችን መግደላቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ሰላማዊ ዜጎች ከፍርድ ቤት ውጪ በአደባባዮች ላይ መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ መግለጫ አውጥታል።

ኮሚሽኑ በሪፖርቱ በአማራ ክልል ጎንደርና ሸዋሮቢት በርካታ አካባቢዎች ከፍርድ ቤት ትዕዛዘው ውጪ ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸውን የሚያመላክቱ መረጃዎች እንደደረሱት ገልጻል።

ተፋላሚ ሀይሎች ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ግጭቶችን እንዲያቆሙ፣ ለሰላማዊ ንግግር ስፍራ እንዲያመቻቹና ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ኮሚሽኑ አክኖም በአማራ ክልል ያለው ግጭት በሰብዓዊ መብቶች ላይ እያሳደረ ያለውን ተፅዕኖ እየተከታተለ መሆኑን ገልጾ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመደንገጉ በፊትና በኋላ ከአዲስ አበባና ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መረጃዎችን እከተቀበለ እንደሆነም አስታውቋል።

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከባድ የመድፍ ተኩስ ጭምር ጥቅም ላይ የዋለባቸው ከፍተኛ ውግያዎች  እየተካሄዱ መሆኑንም ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ላይ ጠቅሷል።

ውጊያው ንጹሀን ዜጎችን ከጉዳት ባልጠበቀ መልኩ በሙካሄድ ላይ ሙሆኑን ተከትሎ ሰላማዊ ዜጎች ህይወታቸውን እያጡ ነውም ብሏል።

ኮሚሽኑ በሪፖርቱ መንገድ ለመዝጋት የሞከሩ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ጭምር መገደላቸውን ፣ እስር ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች መሰበራቸውን፤ የጦር መሣሪያዎችና ጥይቶች ከመዘረፋቸው ባለፈ በቅድመ ፍርድ ያሉ እና ታራሚዎችም አመልጠዋል ብላል፡፡

በአማራ ክልል መንግስት ስር ያሉ በተለያዩ የስልጣን እርከን ላይ ያሉ አመራሮች መገደላቸውንም ኢሰመኮ በሪፖርቱ ላይ ጠቅሷል።

በተለያዩ አካባቢዎች  እንደ ኤሌክትሪክ ሐይል፣ ውሃ፣ ባንክ፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሰልክ፣ ኢነንተርኔት ያሉ መሠረታዊ አገልገሎቶች መቋረጣቸው በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል።

በደብረ ብርሃን ከተማ ለሁለት ቀናት፣ በአራት ብዙ ህዝብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች በተካሄደ ከፍተኛ ውግያ በሆስፒታል፣ ቤተ ከርስቲያን፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በስራ ቦታዎች ያሉ ሰለማዊ ሰዎች በመድፍና ተኩስ ልውውጥ እንደተገደሉ ኢሰመኩ በመግለጫው ላይ ጠቅሳል።

ከደብረብርሃን በተጨማሪም በፍኖተ ሰላም እና ቡሬ ከተሞች በተፈጸሙ የአየር ላይ ጥቃቶች ሰላማዊ ሰዎች ሲገደሉ ጥቃቱም በመኖሪያ ቤቶችና ሕዝብ በሚበዛበቸው ስፍራዎች መፈጸሙን ተከትሎ የጉዳት መጠኑ ከፍ ማለቱ ተገልጿል።

እንዲሁም በባህርዳር ከተማ በርካታ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰዎች በየጎዳናውና ከቤታቸው ውጪ ተግደለዋል ያለው ኮሚሽኑ ወጣቶች ለመደብደብና ለመግደል ፍለጋ ሲደረግ እንደነበረ የሚያመላክቱ ተዓማኒ መረጃዎች ደርሰውኛልም ብሏል።

ኮሚሽኑ በሪፖርቱ እንዳለው የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ ከአማራ ክልል ውጪ በአዲስ አበባ በሚኖሩ የአማራ ማንነት ባላቸው ሰዎች ላይም መፈጸማቸውን አክሏል።

በመሆኑም የፌደራሉ መንግስት የጅምላ እስርን እንዲያቆም፣ ከህግ አግባብ ውጪ የታሰሩ ዜጎች እንዲፈቱ፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ታሳሪዎችን እንዲጎበኙ እንዲፈቅድ ሲል አሳስባል።

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት፣ አሜሪካ፣ ብሪታንያ እና በርካታ ሀገራት በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች እየተፈጸሙ ያሉ የጸጥታ ችግሮች እንዳሳሰባቸው መናገራቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም በአማራ ክልል በሚንስትሮች ምክር ቤት የተጣለው የስድስት ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቆይታ ጊዜ እንዲያትር አሳስባል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚንስትሮች ምክር ቤት የተጣለውን የስድስት ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጊዜ ከአንድ ወር እንዳይረዝም ኮሚሽኑ ባሳለፍነት ሳምንት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *