አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊልሞች እና የቴሌቭዥን ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመሳተፍ እውቅናን ያተረፈው አርቲስት አብነት ዳግም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት አብነት ለረዥም ጊዜ በከባድ የስኳር በሽታ ታምሞ የቆየ ሲሆን፤ ትናንት ሕመሙ በርትቶበት ወደ ጤና ጣቢያ ቢወሰድም ሕይወቱን ማዳን ሳይቻል በመቅረቱ ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል፡፡

አርቲስት አብነት አሉላ አባነጋ፣ የቼዝ ዓለም፣ ዳኛው፣ እስረኛው ንጉስ እና ነቅዕ ቴአትሮች ላይ ተውኗል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አያስቅም፣ አንድ እድል፣ ላምባዲና፣ ሰበበኛ፣ ባንቺ የመጣ፣ ቁልፉን ስጭኝ፣ የነገርኩሽ እለት፣ ፍቅር እስከ መቃብር እና አትሸኟትም ወይ በተሰኙ ፊልሞች ላይ በመተወን አድናቆትን አግኝቷል።

ስንቅ ፣መለከት፣ ትርታ እና ለወደዱት ደግሞ የተሳተፈባቸው ቲቪ ድራማዎች ሲሆኑ፤ በግሉም የቅብብሎሽ ድራማን ደርሷል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *