መንግሥት ከአማራ ክልልል ጋር በተያያዘ ታዋቂ ግለሰቦችን ሳይቀር እያሰረ እንደሆነ ተገለጸ

ከታዋቂ ሰዎች መካከል አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ድምጻዊ ዳኜ ዋለ ዋነኞቹ ናቸው።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በመወከል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የኾኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ታውቋል።

አቶ ክርስቲያን በህ/ተ/ም/ቤት ያለመከሰስ መብት ያላቸው ቢሆንም በፖሊስ ታስረዋል ተብሏል።

ፖሊስ አቶ ክርስቲያንን ለምን እንዳሠራቸው ያልገለጸ ሲሆን የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ዶ/ር ካሳ ተሻገር እና ድምፃዊ ዳኜ ዋለም መታሰራቸው ተሰምቷል።

ይህ በዚህ እንዳለም የመንግስት ኮሙንኬሽን ሚንስትር
ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በአማራ ክልል ያለውን የጸጥታ ችግር የሚያባብሱ ተናግረዋል ።

ሚንስትሩ አክለውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በዋናነት በአማራ ክልል ላይ የሚተገበር ቢሆንም፤ በየትኛው የአገሪቱ ክፍል መንግሥት የሚያደርገውን የሕግ ማስከበር ተግባር ለማስተጓጎል የሚደረጉ እንቅስቃሴ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም በቀናቶች ውስጥ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል እንደሚጸድቅም ገአስረድተዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *