የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለኢትዮጵያና 84 ሚሊየን ዶላር ሰጠ

ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለስንዴ ምርትና ምርታማነት ማሻሻያ የሚውል የ84 ነጥብ ሶስት  ሚሊየን ዶላር (4. 5 ቢሊየን ብር) የልማት ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ከልማት ደጋፋ ውስጥ 54 ሚሊየን ዶላር ከአፍሪካ ልማት ፈንድ፣ 20 ሚሊየን ዶላር ከኔዘርላንድ መንግሰት፣ እንዲሁም 10 ነጥብ ሶስት ሚሊየን ዶላር ደግሞ ሌሎች ድርጅቶች ሰጥተዋል።

የልማት ድጋፋ በአነስተኛ እርሻ የስንዴ አምራች ገበሬዎችን ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የሚውል ሲሆን ይህን ዕውን ለማድረግ እንዲቻል ድጋፉ ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የስንዴ ምርት ለማምረት ፣ የገበያ መሰረተ ልማቶችንና ትስስርን ለማሳደግ እንዲሁም በዘርፋ ያሉ ፕሮጀክቶችን ለማስተዳደር የሚውል ነው፡፡

የልማት ድጋፋን ስምምነት በኢትዮጵያ መንግስትን በኩል የገንዘብ ሚነስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እንዲሁም የአፍሪካ ልማት ፈንድን በመወከል ዶ/ር አብዱል ካማራ በምስራቅ አፍሪካ የአፍሪካ ልማት ባንክ ምክትል ዳይሬክተር መፈረማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት ከዓለም ባንክ ጋር የ460 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ስምምነት መፈራረሟ ይታወሳል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *