የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጂማ ዲልቦ በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።
ዳይሬክተሩ ከአራት ዓመታ በላይ ከመሩት ተቋም ስራቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ በመንግስት ተቀባይነት ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ኃላፊ ስራቸውን ለምን እንደለቀቁ ያሉት ነገር የለም።
ጂማ ዲልቦ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ “ዘርፉ ከነበረበት ድባቴ ወጥቶ ለሀገር ልማትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አስተዋጽኦ ማበርከት መጀመሩ በቀጣይ ዓመታት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በጦርነት ምክንያት የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ቁጥር እያደገ የመጣ ቢሆንም በዛው ልክ ግን ሰራተኞቻቸው እየተገደሉባቸው መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ36 በላይ ለተቸገሩ ዜጎች ድጋፍ ለማድረስ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ እንደተገደሉ ተገልጿል።
ከሁለት ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ በጤና ምክንያት ከሀላፊነታቸው ለመልቀቅ ማመልከቻ ማስገባታቸው ይታወሳል