ቴክኖ ሞባይል ካሞን 20 የተሰኘ ምርቱን ይፋ አደረገ

ዋና መቀመጫውን ቻይና ያደረገው ቴክኖ ሞባይል አዲስ የሞባይል ምርቱን ለኢትዮጵያ ደንበኞቹ በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል።

ቴክኖ ሞባይል ይፋ ያደረገው ካሞን 20 አዲስ ምርት የአምስተኛ ትውልድ ወይም 5G ኔትወርክ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ተብሏል።

እንዲሁም ይህ አዲስ ስልክ 8 ጌጋ ባይት ራም እና 256 ጌጋ ባይት መጠን ያላቸው መረጃዎችን የመያዝ አቅም ሲኖረው ለተክም ሰዓት ማስጠቀም የሚያስችል ባትሪም አለው ተብሏል።

ሶስት ካሜራ እንዳለው የተገለጸው ይህ አዲስ የቴክኖ ሞባይል ስልክ ካሳለፍነው ግንቦት ወር ጀምሮ ለደንበኞቹ ቀርቧል።

ቴክኖ ሞባይል በትራንሽን ኩባንያ ስር ሆኖ በፈረንጆቹ 2006 ላይ የተመሰረተ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው።

በጆርጁ ዙ የተቋቋመው ቴክኖ ሞባይል ዋና መቀመጫውን በቻይናዋ ሸንዘን አድርጎ በመላው ዓለም ምርቶቹን ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ መሆኑን አስታውቋል።

ቴክኖ ሞባይል ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት እንዳለው ሲገለጸ ከተንቀሳቃሽ ስልኮች በተጨማሪም ታብሌት፣ የስልክ አክሰሰሪዎች እና ራውተሮችንም በማምረትም ይታወቃል።

ቴክኖ ሞባይል አሁን ላይ በእስያ፣ አፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅላቲን እአሜሪካ እና ምስራቅ አውሮፓ ሀገራት ባሉት ማዕከላት ምርቶቹን ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *