አሜሪካ በኢትዮጵያ ጦርነት 350 ሺህ ሰዎች መገደላቸውን ገለጸች

አሜሪካ ኢትዮጵያን ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጻሚ ሀገርነት ዝርዝር ውስጥ ሰርዛለች።

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ነበር አሜሪካ ኢትዮጵያን የከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጻሚ ሀገር ዝርዝር ውስጥ የመዘገበቻት።

ይህን ተከትሎም ዋሽንግተን ለኢትዮጵያ ታደርጋቸው የነበሩ የልማት ስራዎች ድጋፎችን አቋርጣ ቆይታለች።

እንደ ፎሬይን ፖሊሲ ዘገባ ከሆነ አሜሪካ ኢትዮጵያ አሁን ላይ የከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጸምባት ሀገር አይደለችም የሚል አቋም ላይ ደርሳለች።

በኮሮና ቫይረስ፣ በጦርነት እና በዓለም አቀፍ ንግድ መቀዛቀዝ ምክንያቶች ኢትዮጵያ እንደ ሌሎች ሀገራት የብድር መክፈያ ጊዜ ሽግሽግ እንዲደረግ አስቀድማ ጠይቃ ነበር።

ይሁንና አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በጣለችው እገዳ ምክንያት ዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍ ለብዙ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ያደረጉትን የገንዘብ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ማድረግ እንዳልቻሉም ተገልጿል።

የዋሸንግተን የአሁኑ ውሳኔም ሲጓተት የቆየውን የኢትዮጵያ የብድር መክፈያ ሽግሽግ እና አዳዲስ የብድር እና የገንዘብ ድጋፎች እንድታገኝ እድል ይፈጥራልም ተብሏል።

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ፍላጎት እንዲሳካ ቁልፍ አጋር ተደርጋ የምትታይ ሲሆን በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተው ጦርነት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ጎድቶት ቆይቷል።

በርካታብ የዓለማችን ተቋማት በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት ከ600 ሺህ በላይ ዜጎችን ህይወት እንደቀጠፈ ይገልጻሉ።

አሜሪካ ደግሞ ይህ ጦርነት የ350 ሺህ ዜጎችን ህይወት እንደቀጠፈ ታምናለች ሲል ፎሬይን ፖሊሲ በዘገባው ላይ ጠቅሷል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *