ኢትዮጵያ የቀድሞ የባህር ሀይል የውጊያ ጀልባዎችን ለግዳጅ ዝግጁ አደረገች

ወደብ አልባ የሆነችው የኢትዮጵያ መከላከያ ዋና አዘዥ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፈጣን ተዋጊ ጀልባዎችን ጎብኝተዋል፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአየር ኃይል አቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከል ወደ አገልግሎት የመለሳቸውን ፈጣን ተዋጊ ጀልባዎችን እንደጎበኙ የሀገር መካለከያ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።

ተዋጊ ጀልባዎቹ በቀድሞ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አገልግሎት የሠጡ ሲሆን ዳግም የባሕር ኃይሉን ዝግጁነት ያጠናክራሉም ተብሏል።

የአየር ኃይል አቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከል ከ30 አመት በላይ ተገለው እና አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ጀልባዎችን የፈጣን ተዋጊ ጀልባ ቴክኖሎጂ እና መሳሪያዎች በመግጠም ለግዳጅ ዝግጁ መደረጋቸውም ተገልጿል።

ኢትዮጵያ የባህር ሀይልን እንዳዲስ በማደራጀት ላይ መሆኗን ከሁለት ዓመት በፊት መግለጿ ይታወሳል፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ አካል የሆነችው ኤርትራ ከ30 ዓመት በፊት በህዝበ ውሳኔ ከመገንጠሏ በፊት የራሷ ወደብ እና ባህር ሀይል የነበራት ሲሆን አስመራ ከተገነጠለች በኋላ ግን ወደብ አልባ እና የባህር ሀይሏንም በትና ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአምስት ዓመት በፊት ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ግን የሀገር መከላከያ ሰራዊት የባህር ሀይልን እንደ አዲስ በማደራጀት ላይ ይገኛል፡፡

የባህር ሀይልን ለማደራጀትም ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ጋር ወታደራዊ ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ ፈረንሳይ ከዚህን ስምምነት መውጣቷን አስታውቃለች፡፡

ይህን ጦርነት ያስቆመው የሰላም ስምምነት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ መፈረሙን ተከትሎ ፈረንሳይ ወደ ስምምነቱ ስለመመለሷ እስካሁን በይፋ አልተገለጸም፡፡

ይህ የሑለትዮሽ ስምምነት ኢትዮጵያ የባህር ሃይል አባላትን ስልጠና መስጠት፣ የጦር መሳሪያ ግዢ እና ሌሎች ወታደራዊ ትብብሮችን ማድረግን ያካተተ ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባለፉት ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ ፓሪስ አምርተው ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር መክረዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *