የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ከሓላፊነት ለቀቁ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ከሓላፊነት ለቀቁ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ዓለም አቀፍ ጨረታ ማሸነፉን ተከትሎ ነበር አንዋር ሶሳ ወደ አዲስ አበባ የመጡት።

ከ2019 ጀምሮ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን በስራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የቆዩት አንዋር ሶሳ አሁን ላይ ከሀላፊነት መነሳታቸውን ድርጅታቸው አስታውቋል።

ይሁንና ሳፋሪኮም ለምን አንዋር ሶሳን ከሀላፊነት እንዳነሳቸው እስካሁን ይፋ አላደረገም።

ከአንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎቶችን መስጠት የጀመረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአጭር ወራት ውስጥ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን እንዳፈራ አስታውቋል።

የኔትወርክ አገልግሎቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም በመከራየት ደንበኞችን እያገለገለ የሚገኘው ሳፋሪ ኮም የኢትዮጵያ ገበያው ያሰበውን ያህል እንዳልሆነለት ከዚህ በፊት መግለጹ አይዘነጋም።

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን መሾሙ ይታወሳል።

ላለፉት ሶስት ዓመታት በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አዲስ ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

አምባሳደር ሔኖክ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳዮች ግንኙነት እና ቁጥጥር ሀላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *