ኢትዮጵያ ከኮቲዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆነች

በኮቲዲቯር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች በመካሄድ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዚህ ማጣሪያ ጨዋታ አንድ አካል የሆነው ጨዋታ ከማላዊ አቻው ጋር አድርጓል።

ይህ ጨዋታ ዜሮ ለዜሮ በሆነ አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኮቲዲቫሩ የአፍሪካ ዋንጫ መውደቁን አረጋግጧል።

ምድቡን እየመራች ያለችው ግብጽ አስቀድማ ማለፏን ያረጋገጠች ሲሆን ጊኒ ደግሞ ሁለተኛ በመሆን ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፏን አረጋግጣለች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት ውበቱ አባተ በውጤት ማጣት መሰናበታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከአሰልጣኝ ውበቱ ጋር በስምምነት እንደተለያየ ከዚህ በፊት አስታውቋል።

በያዝነው ዓመት ለሚካሄደው የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ኮቲዲቯርን ጨምሮ ከ15 በላይ ሀገራት ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

ኮቲዲቯር፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽ፣ ዛምቢያ፣ ቱኒዝያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ሴኔጋል፣ አልጀሪያ እና ሞሮኮ ዋነኞቹ ሀገራት ናቸው።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *