ኢትዮጵያ የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ ሂዩማን ራይትስ ዋች በትግራይ ክልል ተፈጸመ በሚል ያወጣውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት እንደማትቀበለው አስታውቃለች።

በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የሰላም ስምምነት ቢፈረምም አሁንም በትግራይ ምዕራባዊ አካባቢዎች የሚካሄደው የዘር ማጽዳት ወንጀል መቀጠሉንና የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላትም ለፈጸሙት ግፍ ተጠያቂ አልተደረጉም በማለት ሂዩማን ራይት ወች ከሰሞኑ ያወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ መንግስት ምላሽ ሰጥቷል፡፡

መንግስት በምላሹም ሪፖርቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ጉልህ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚገልጽ መሰረተ ቢስ ሪፖርት ነው ሲል ተችቷል።

አክሎም በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል የነበረው ግጭት በርካታ አካባቢዎችን ለጉዳት ያጋለጠ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ የተወሰነ አካባቢን መርጦ ደጋግሞ ሪፖርት በማዘጋጀት በሰብዓዊ መብት አጀንዳ ሽፋን የተለየ የፖለቲካ ተልዕኮዉን ለማሳካት ዓላማ ያደረገ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ሲል ገልጧል፡፡

የመብት ጥሰት ተፈጽሟል ለማለት የቀረበው ሪፖርት ይዘት ሲታይም ተገቢው ምርመራ ያልተደረገበት እና በበቂ ማስረጃ ያልተደገፈ ከመሆኑ አንጻር እምነት የሚጣልበት አይደለም ብሏል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *