ከፊሊፒንስ ጋር የተጣላችው ኩዌት ኢትዮጵያዊያንን እንደምትቀጥር ገለጸች

በነዳጅ የበለጸገችው የመካከለኛው መስራቅ ሀገር ኩዌት የሦስት ወራት አስገዳጅ ስልጠና የወስዱ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ለመቀበል ከመንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መድረሷ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እና ኩዌት መንግሥታት በኩል መግባባት ላይ መደረሱን ተከትሎም፤ በጥቂት ቀናት ውስጥ የጋራ የሥራ ስምምነት እንደሚፈረም አረብ ታይምስ ዘግቧል።

ከስምምነቱ በኋላ በኢትዮጵያ የሚገኙ 600 የሚሆኑ የሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሰው ኃይል በማቅረብ ይሰራሉም ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያን ሰራተኞች ቢያንስ ብቃቱ ከተረጋገጠ ተቋም የ3 ወር ስልጠና መውሰድ በግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡

ኩዌት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የቤት ሰራተኞች የምታገኘው ከፊሊፒንስ ሲሆን፤ በኹለቱ አገራት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ አገሪቱ የሰራተኛ እጥረት በማጋጠሙ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ለመቀበል ማቀዷ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከኩዌት መንግሥት ጋር በተስማሙት መሰረት፤ አንድ ሰራተኛ በወር 90 ኩዌት ዲናር ወይም 300 ዶላር ይከፈለዋል የተባለ ሲሆን፤ ይህም በወቅታዊው የምንዛሬ ተመን ወደ 16 ሺሕ የኢትዮጵያ ብር ይጠጋል፡፡

ወደ ፊትም ወርሃዊ ክፍያዉ እስከ 500 ዶላር ከፍ ሊል እንደሚችልም የተገለጸ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም ኩዌትን ጨምሮ ከቤሩት፣ ከእስያ እና አውሮፓ አገራ ጋር የስምምነት ሥራዎች እንደተጀመሩ መግለጹ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ሰራተኞችን በማቅረብ ጥሩ ልምድ ያላት ሲሆን በሳውዲ አረቢያ ብቻ በዚሕ አመት 500 ሺህ ዜጎችን የመላኩ ሰ

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *