የተመድ ፈንጅ አምካኝ ቢሮ በትግራይ ክልል ቢሮ ሊከፍት መሆኑን አስታወቀ

በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ መቆሙ ይታወሳል፡፡

በዚህ ጦርነቱ ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ አገልግሎቶች ወደ ነበሩበት እንዲገቡ የማድረግ ስራ በፌደራል እና ክልል መንግስታት እየተሰራም ይገኛል፡፡

ይሁንና በጦርነቱ ወቅት በየቦታው ተቀብረው የነበሩ ፈንጂዎች ትምህርትን እና ሌሎች አገልግሎቶችን ማስቀጠል አልቻሉም ተብሏል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ፈንጂ ማስወገድ አገልግሎት (UNMAS ትግራይ ክልልን ጨምሮ በሰሜን ኢትዮጵያ ቦታዎች ያሉ ፈንጂዎችን እና ሌሎች የጦር መሣሪያ ቅሪቶችን የማስወገድ ተልዕኮ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ፈቃድ ተሰጥቶታል ተብሏል፡፡

እንደ አፍሪካ ህብረት መግለጫ ከሆነ ፈንጂዎችና ሌሎች ያልፈነዱ የጦር መሣሪያ ቅሪቶች ጦርነት በተካሄደባቸው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች፣ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እያደረሱ በመሆኑ አካባቢዎችን ከፈንጂዎች ለማጽዳት እንዲቻል፣ የተመድ ፈንጂ ማስወገድ አገልግሎት በመሰማራት ላይ ይገኛል፡፡

የተመድ ፈንጂ ማስወገድ አገልግሎት በቅርቡ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ቢሮውን እንደሚከፍትና ዋና መቀመጫውን በመቐለ አድርጎ በሁሉም ጦርነቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ኃላፊነቱን ለመወጣት እንደሚሰማራ ተነግሯል።

በዚህ ወር በአፋር ክልል በፈነዳ የወደቀ የሞርታር ጥይት የአራት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን በትግራይ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 300 በሚሆኑት ውስጥ በርካታ የጦር መሳሪያ ቅሪቶች ተገኝተዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሁለት ዓመታት በተካሄደውን ጦርነት ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ማድረሱ ባሳለፍነው ሳምንት መገለጹ ይታወሳል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴርን በዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱ ላይ እንዳለው ለሁለት ዓመት የዘለቀው ጦርነት 28 ቢሊዮን ዶላር አውድሟል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *