ቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የስኳር ፋብሪካ ሊገዙ ነው

የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለጸጋው ናይጀሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የስኳር ፋብሪካ ለመግዛት እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት በይዞታው ስር ያሉ የስኳር ፋብሪካዎችን መሸጥ እንደሚፈልግ መግለጹ ይታወሳል።

በዚህ መሰረትም የስኳር ፋብሪካዎችን የመግዛት ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ፍላጎታቸውን እንዲያሳውቁ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ናይጀሪያዊው የአፍሪካ ቀዳሚ ቢሊየነር ፍላጎታቸውን ከገለጹ ባለሀብቶች መካከል አንዱ መሆናቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ፋብሪካ ያላቸው አሊኮ ዳንጎቴ አሁን ደግሞ የስኳር ፋብሪካ የመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

ከአሊኮ ዳንጎቴ በተጨማሪም ኮካ ኮላ ኩብንያም በኢትዮጵያ የስኳር ፋብሪካ ለመግዛት ከሚፈልጉ የቢዝነስ ተቋማት መካከል አንዱ ነው ተብሏል።

የገንዘብ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ሰዎች በዚህ ሳምንት የስኳር ፋብሪካዎቹን ጨረታ በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ለፋብሪካዎቹ የወጣውን ጥሪ ተከትሎ ከ20 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ወገኖች ፍላጎታቸውን እንዳሳዩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ስምንቱን የስኳር ፋብሪካዎች መግዛት ለሚሹ ኩባንያዎች ፍላጎታቸውን እንዲያሳውቁ ጥሪ ያቀረበው በነሐሴ 2014 ነበር።

ለሽያጭ ከቀረቡት የስኳር ፋብሪካዎች መካከልም አርጆ ዴዴሳ፣ ከሰም፣ ጣና በለስ እና ተንዳሆ የስኳር ፋብሪካዎች ዋነኞቹ ናቸው።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *