የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ለሁለት ዓመታት በዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በትግራይ ክልል ስላደረሰው ውድመት ግንቦት መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የአስተዳደር በደል መከላከል ዳይሬክተር አዳነ በላይ በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ከ2ሺህ በላይ መምህራን እና ከ 1 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች መገደላቸው ተረጋግጧል ብለዋል።
ተቋሙ በሰጠው መግለጫ በትግራይ ክልል ብቻ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን በሁሉም የማበረሰብ ክፍል ላይ ጦርነቱ ውድመት ማድረሱ ተገልጿል።
በዚሁ ጦርነት ምክንያት 88 በመቶ የመማሪያ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባለ ሲሆን 60 በመቶ የመማሪያ መፃሕፍት ደግሞ ከጥቅም ውጪ ሆነዋል ተብሏል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ የጦርነቱ ዳፋ መሠረተ ልማቶቹን በማውደም እና ከጥቅም ውጭ በማድረግ እንዲሁም የትምህርት ስርዓቱን ወደ ኋላ በመመለስ ብቻ እንዳልተመለሰ ገልፀው “በሺዎች የሚቆጠሩ መምህራንና ተማሪዎችን ገድሏል።
ባሳለፍነው ጥቅምት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረሠውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የትምህርት ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት የጉዳት መጠናቸውን የልየታ ስራ እየተሰራ ይገኛል።