ማንችስተር ሲቲ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን አሸነፈ

አጓጊው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሊጠናቀቅ አንድ ጨዋታ ብቻ ቀርቶታል።

ማንችስተር ሲቲ ቀሪ ሁለት ጨዋታ እየቀረው የ2022/23 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን አሸንፏል።

የዘንድሮውን ውድድር ሳይጠበቅ ለረጅም ወራት ሲመራ የቆየው አርሰናል ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ እርግጥ ሆኗል።

አርሰናል በትናንትናው ዕለት ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረገውን ጨዋታ መሸነፉን ተከትሎ በፔፔ ጋርዲዮላ የሚሰለጥነው ማንችስተር ሲቲ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት ዋንጫ መብላቱን አረጋግጧል።

ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ለማለፍ የሚደረገው ትንቅንቅ እንደቀጠለ ሲሆን ሊቨርፑል በአስተንቪላ መሸነፉ የተሳትፎ ተስፋውን አክስሟል።

ከቦርንማውዝ የተጫወተው ማንችስተር ዩናይትድ በካዝሚሮ ብቸኛ ጎል ማሸነፉን ተከትሎ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ተስፋውን የበለጠ አለምልሟል።

ከፕሪሚየር ሊጉ ላለመውረድ እየተደረገ ያለው ትንቅንቅ የቀጠለ ሲሆን ሳውዛምፕተን ወደ ታችኛው ሊግ መውረዱን አረጋግጧል።

ሊድስ ዩናይትድ፣ ኤቨርተን፣ ሌቺስተር ሲቲ እና ኖቲንግሀም ፎረስት ደግሞ ወደ ታችኛው ሊግ ላለመውረድ ትንቅንቅ በማድረግ ላይ ያሉ ክለቦች ናቸው።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *