የኢትዮጵያ የውጭ እዳ 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የውጭ እዳ 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥ ባንኮች የተበደረችውን ሳይጨምር ከውጭ አበዳሪ ምንጮች ተበድራ ያልመለሰችው የዕዳ መጠን 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል።

እንደ ሚኒስቴሩ ሪፖርት ከሆነ ኢትዮጵያ ካለባት 28 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ውስጥ 54 በመቶ የተገኘው ከዓለም ባንክና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ነው፡፡

46 በመቶው ደግሞ ከቻይና እና ከሌሎች ውጭ የግል አበዳሪ ተቋማት የተገኘ እንደሆነ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ባለባት ከፍተኛ የውጭ ዕዳ ብድር ምክንያትም በዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ምደባ ከፍተኛ የዕዳ ጫና ያለባቸው አገሮች ዝርዝር ውስጥ ተመድባለች።

በተያያዘ ዜና ኢትዮጵያ ከሶስት ዓመት በፊት የቡድን 20 አገሮች የዕዳ ጫናን ለማቅለል ባዘጋጁት የዕዳ መልሶ ማዋቀር ሥርዓት ለመጠቀም ጥያቄ አቅርባ ነበር።

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በኮሮና ቫይረስ፣ በጦርነት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ምክንያቶች ያቀረበችው የእዳ መክፈያ ጊዜ ይሸጋሸግልኝ ጥያቄ በአሜሪካ ምክንያት እንደዘገየ ታውቋል።

ኢትዮጵያ በቡድን 20 አገሮች የዕዳ መልሶ ማዋቀር ሥርዓት ለመጠቀም ያቀረበችው ጥያቄ ምላሽ የዘገየው በአሜሪካ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ይህን ለማቃለል በቡድን 20 አገሮች የተሰናዳውን የውጭ ዕዳ ጫና ማቅለያ ለመጠቀም ጥያቄ ብታቀርብም ለዓመታት ጥያቄው ምላሽ ሳያገኝ ዘግይቷል፡፡

ስለዚሁ ጉዳይ በዋሸንግተን በዓለም ገንዘብ ድርጅት እና በዓለም ባንክ የ‹‹ስፕሪንግ›› ጉባዔ የተናገሩት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ሒደቱ ከመዘግየቱ ባለፈ ጥያቄዋን ከማቅረቧ ጋር በተያያዘ ብቻ የአገሮችን ዕዳ የመክፈል አቅም በሚለኩ ዓለም አቀፍ ደረጃ አውጪዎች የመክፈል አቅም ደረጃዋ ዝቅ እንዲል መደረጉን አስረድተዋል።

በዚህም ምክንያት ለአውሮፓ አገሮች የሸጠችው ዩሮ ቦንድ ግብይት መቀዛቀዙንና የአበዳሪዎችን እምነት መሸርሸሩንም አቶ አህመድ አክለዋል።

ኢትዮጵያ በቡድን 20 አገሮች የዕዳ መልሶ ማዋቀር ሥርዓት ለመጠቀም ያቀረበችው ጥያቄ ምላሽ የዘገየው ጉዳዩ የሚመለከታቸው የአሜሪካ መስሪያ ቤቶች ከስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ነው፡፡ 

በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው ጦርነት ፣ ኢትዮጵያ ከቻይና የተበደረችው ብድር መጠን ግልጽ አለመሆን እና በሌሎች ምክንያት አሜሪካ በኢትዮጵያ ጥያቄ ዙሪያ ምላሽ አለመስጠቷ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የእዳ ሽግሽግ የገንዘብ ነክ ጉዳዮች በዋነኛነት የሚገመገመው በአገሪቱ ግምጃ ቤት ሲሆን፣ ስቴት ዲፓርትመንት እና የደህንነት ተቋማት ሌሎቹ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ናቸው፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *