በሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት ሙሽራው እና አባትየው ተገደሉ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን በቋሪት ወረዳ ወይበኝ ቀበሌ ልዩ ቦታው በተለምዶ አነሳት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ በተዘጋጀ ሰርግ ላይ የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

በባህሉ በወጉ መሰረት ልጃችንን ለልጃችሁ ተባብለው ሙሽሪትና ሙሽራው ሊጣመሩ የሙሽራው ቤተሰብና የሙሽሪት ቤተሰብ በስጋ ዝምድና ሊጣመሩ ቤት ባፈራው እንደአቅም ድግስ በመደገስ የሩቁና የቅርቡ ወዳጅ ዘመድ ልጃችንን ስለምንድር ልጃችንን መርቁልን ማለት የተለመደ ስርዓትና ወግ ነው፡፡

በትናንትናው ዕለት ማለትም ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ለሰርጉ ድምቀት የተጠራው ወዳጅ ዘመድ በተሰበሰበበት ወደ ቤታቸው ሊወጡ ሲሉ የደስ ደስ ጥይት ይተኮሳል።

በዚህ ሰዓትም በተተኮስ ጥይት ሙሽራው እና የሙሽራው አባት ወዲያውኑ ህይታቸው ማለፉ ተገልጿል።

እንዲሁም አንድ የሴት ሚዜ አና ሰርጉን ለማድመቅ የተገኙ 4 ሰወች በድምሩ አምስት ሰዎች ደህሞ መቁሰላቸውን የዞኑ ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ በወንጀል ድርጊት የተሳተፉትን በቁጥጥር ስር አድርሆ  ምርመራ እያጣራ መሆኑም ተገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *