ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝቷል።
ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ የቴሌኮም ኩባንያ አሁን ደግሞ ተጨማሪ ፈቃድ ማግኘቱን አስታውቋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኤምፔሳ አማካኝነት የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝቷል።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ባንኩ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድን ለሳፋሪ ኮም መስጠቱን አስታውቀዋል፡፡
ይህም ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የውጭ አገር ኩባንያ እንደሚያደርገው የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል፡፡
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን አዲስ ሀላፊነት መስጠቱ ይታወሳል።
አምባሳደር ሔኖክ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳዮች እና ቁጥጥር ሀላፊ ሆነው የተሸሙ ሲሆን የቀድሞውን የድርጅቱ መሪ የነበሩት ማቲው ሀሪሰንን ተክተዋል።
አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ ከ2018 እስከ 2022 ድረስ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከ20 በላይ ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን በቅርቡም በኤምፔሳ አማካኝነት የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ እንደሚያገኝ ተገልጿል።