አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺህ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ ወይም ዲቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ ታስገባለች።
ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት ላይ በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ድቪ ሎተሪ አሸናፊዎች መታወቃቸው ተገልጿል።
የዲቪ 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎችም መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ከሚያዚያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በትዊተር ገጹ ጽፏል።
ኢምባሲው አክሎም በዲቪ ሎተሪ ድረገጽ ላይ በመግባት አመልካቾች ያመለከቱበትን ልዩ ቁጥር ወይም ኮድ በማስገባት ማወቅ ይችላሉም ብሏል።
ይህ በዚህ እንዳለም የዲቪ ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁም አሳስቧል።
ለዲቪ ሎተሪ ስለማሸነፋቸው እና አለመድረሱን አመልካቾች በራሳቸው እጃቸው ላይ ባለው ሚስጢራዊ ቁጥር ማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ እንደሆነም ተገልጿል።
የ2023 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች እስከ ቀጣዩ መስከረም 2016 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንደሚስተናገዱም ኢምባሲው በመግለጫው ላይ ጠቁሟል።
የ2022 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መከሰቱን ተከትሎ የአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት በመሻከሩ ተጎድተናል ማለታቸው ይታወሳል።
I was looking through some of your articles on this website and
I conceive this site is real informative! Keep on putting up.Raise blog range