በ20 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት የተወሰነላቸው ጋዜጠኞች ፌደራል ፖሊስ በሌላ ወንጀል እንደሚጠረጥራቸው አስታውቋል፡፡
ከ15 ቀን በፊት የታሰሩት ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ታዎድሮስ አስፋው በአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያና በሽብርተኝነት ተጠርጥረዋል።
ጋዜጠኞቹ ከሰሞኑ ፍርድ ቤት ቀርበው በ20 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ቢሆንም ፌደራል ፖሊስ በአዲስ ወንጀል እንደሚጠረጥራቸው ለፍርድ ቤት ባቀረበው ማመልከቻ ጠይቋል፡፡
አዲሱ የፌደራል ፖሊስ የፍርድ ቤት ማመልከቻ እንደሚያስረዳው ጋዜጠኞቹ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጪ ሀገር የገቢ ማሰባሰቢያ መንገድ በመዘርጋት ዜጎች ለሽብር እና አመጽ እንዲነሳሱ ቀስቅሰዋል ይላል፡፡
በዚህም መሰረት ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ተጠርጣሪዎቹ ለተጨማሪ 15 ቀናት ታስረው እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡
ከፌደራል ፖሊስ ምርመራ ቢሮ ማመልከቻ የቀረበለት የልደታ ምድብ ችሎትም ተጠርጣሪዎቹ ለ14 ቀናት ታስረው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡