ድርጅቱ ድጋፉን ያገኘው በግል ባለሀብት ከሚንቀሳቀሰውና በደቡብ ሰሀራ ሀገራት በቴክኖሎጂ ላይ ከሚሰራው ከኮንቨርጀንስ ፓርተንርስ እና ከ14 ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ልማት ላይ ከሚሰሩ ታዋቂ የገንዘብ ተቋማት ነው።
በቅርቡ በዲጂታል የመሰረተ ልማት ላይ ስራዎች የገንዘብ አቅርቦት ፕሮጅክቱን በ 296 ሚልየን የአሜሪካ ዶላር ያጠናቀቀው 42 ማርኬትስ ግሩፕ ለተጠቃሚዎች ወይም ለንግድ ድርጅቶች የገንዘብ ልውውጥ ላይ ከሚሰራው ፊንቴክ ቡድን ወስጥ አንዱ ቡድን ነው።
የ 42 ማርኬትስ ግሩፕ ስራ አስኪያጅ አንድሪስ ብሪንክ እንዳሉት “የተገኘው ገንዘብ ድጋፍ የዲጂታል ገንዘብ መሰረተልማቱ ትክክለኛ መተማመኛ እንዲያገኝ ከማድረጉ ባሻገር ለቀዘቀዘውም ሆነ እያደገ ለሚመጣ ገበያ በጎ የኢንቨስትመንት ተፅዕኖ እንዲኖረው ያደርጋል” ብለዋል።

ከ42 ማርኬትስ ግሩፕ የበሰሉ ስራዎች ከሚሰሩት ድርጅቶች መካከል የካፒታል እና ገበያ አገልግሎቶች የሚሰጥና የሚያማክረው አንድሊ (UK, andile.net) የተባለ ድርጅት ነው ተብሏል፡፡
የተረጋጋ እና ብዙ ገበያ ያላቸው እንዲሁም የኢንደስትሪ ባለሙያዎች የግምጃ ቤት እና የንግድ ከፍላቸውን እንዲረዱ እና እዛው ካሉ ባንኮች ጋር እንዲተሳሰሩ የአይቲ ኦፕሬሽኖቻቸውን በማቀላጠፍ እና በራስ-ሰር እንዲሰሩ የሶፍትዌራቸውን ከዘመኑ ጋር እንዲያዘምኑ እየሰራ ይገኛል።
የአንድሊ መሠረተ ልማት ንግዱ በአሁኑ ጊዜ በመላው አፍሪካ፣ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአውሮፓ ህብረት፣ በአውስትራሊያ እና በህንድ በሚገኙ የኢንቨስትመንት ባንኮችን እና ማዕከላዊ ባንኮች ላይ እየሰራ ይገኛል።
ሌላኛው የግሩፑ ኩባንያ በቅድሚያ የንግድ ስራ ላይ መዋቅር ዘርግቶ የሚሰራው ኤፍኤክስፍሎው (SA, fxflow.co) ሲባል ቁጥጥር ባለው ገበያ ላይ አስመጪ እና ላኪዎች ለኪሳራ እና ለአደጋ ተጋጭነታቸውን በመቀነስ እሴት እንዲጨምሩ የሚሰራ ኩባንያ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ሜሽ (Netherlands,Mesh.trade) የተባለው ሌላው የግሩፑ ኩባንያ ሲሆን በተቋም ደረጃ፣ ያልተማከለ፣ ባለብዙ ጎን የፋይናንሺያል ገበያ መድረክ ሲሆን ልየነታቸውን ለማጥበብ እና ለማቀራረብ ከሚሰራባቸው ስራዎች መሀል ; TradFi (የፋይናንሺያል እና የካፒታል ገበያዎች ከ ባህላዊ ዓለም ጋር ባላቸውን ልዩነቶች ላይ)፣ AltFi (የተለዋጭ አማራጭ፣ በተለምዶ ሕገወጥ የፋይናንስ ንብረቶችን ከኢንቨስትመንት መሳሪያዎች ጋር ) እና DeFi (አዲሱ) የተከፋፈለው ሌዠር ቴክኖሎጂን ከቶኬኖሚክስ ዓለም) ጋር ይገኝበታል።
የኮንቨርጀንስ ፓርትነርስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብራንደን ዶይል እንዳሉት – “ይህ በፋይናንሺያል ገበያዎች ዲጂታል ለውጥ ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ ኢንቨስትመንቶች ስራዎቻችን ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ ቦታ 42 ማርኬትስ ግሩፕ እንደ ጀማሪ አሸናፊ ሆኖ እያየን ነው ።
የቀድሞ ስራዎቻቸው የዚህ የቡድን ኩባንያዎች ተከታታይነት ያለው ባለ ሁለት አሃዝ እድገት ፣ በካፒታል ገበያ ውስጥ ጥልቅ እውቀት እና ልምድ፣ ጥራት ያለው አመራር ቡድን እንዳላቸው ተረድተናል” ብለዋል።
ሌላው ድጋፍ ያደረጉት አስራ አራቱ የአለም አቀፍ ልማት ፋይናንስ ተቋማት በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና አፍሪካ የሚገኙ ሲሆኑ በኮንቨርጀንስ ውስጥም መዋዕለ ነዋያቸውን የሚያፈሱ ኢንቨስተሮች ናቸው።
ብሪንደን አክለው ሲናገሩ “ይህ ስንፈልግ የነበረው የተገናኘ ካፒታል ነው። በጋራ ለመስራትና ተጨማሪ እድሎችን ለመፈለግ ከእነዚህ ባለሀብቶች ጋር በንቃት እየተሳተፍን ነው” ሲሉም አክለዋል።
በኔዘርላንድ ዓለም ዓቀፍ የልማት ፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የኃላፊነት ቦታ ያላቸው የኢንቨስትመንት ኦፊሰሩ ክርስቲያን ሮኤሎፍሴ በበኩላቸው “የደች የልማት ባንክ የአፍሪካ ሥራ ፈጣሪዎችን በመለየት እና በመደገፍ ኮንቨርጀንስ ከአጋሮች ጋር በሚያደርገው ጥረት ተደስቷል።
“እንደ 42 ማርኬትስ ባሉ ኩባንያዎች ውስጥ በሚያደርጉት ኢንቨስትመንቶች፣ በዲጂታል መንገድ የተሻለ የፋይናንስ ማካተትት በአህጉሪቱ እየጨመረ እንደሚመጣ እናምናለን።
ከኮንቨርጀንስ ፓርትነርስ አጋር በመሆን ለዘመናችን ትልቅ ፍላጎቶች ተገቢ መፍትሄዎችን ከሚያዘጋጁ አዳዲስ ኩባንያዎች ጋር መጣመራችን ኩራት እንዲሰማን አርጓል” ሲሉም ተናግረዋል።