ተመድ በቶርች ጉዳይ ኢትዮጵያን ሊገመግም መሆኑን አስታወቀ

የተባበሩት መንግታት ድርጅት በፈረንጆቹ 1984 ላይ በእስረኞች የሚፈጸሙ ስቃዮችን ወይም ቶርቸርን ለመከላከል በማሰብ ስምምነት አዘጋጅቶ ነበር።

ይህን ስምምነት ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን ሀገራት የተቀበሉት ሲሆን ትግበራው ግን ከቦታ ቦታ ይለያያል።

የዚህ ስምምነት አዘጋጅ የሆነው ተመድ ስምምነቱን የተቀበሉ ሀገራት ህጉን እንዴት እየተገበሩት እንደሆነ ሊገመግም መሆኑን ለዓልዐይን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ፣ ኮሎምቢያ፣ ብራዚል፣ ካዛኪስታን፣ ስሎቫኪያ እና ሉግዘምበርግ ደግሞ የሚገመገሙ ሀገራት ናቸው ተብሏል።

10 አባላት ያሉት የተመድ ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ሀገራቱን በጀኔቫ እንደሚገመግሙም ተገልጿል።

ይህ የባለሙያዎች ቡድንም የጸረ ቶርቸር ህግ ትግበራው ግምገማው የተገምጋሚ ሀገራት ተወካዮች፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት ይገኛሉ ተብሏል።

ግምገማውም ከሚያዚያ 9 ቀን እስከ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በስዊዘርላንድ ጀኔቫ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በተመድ የጸረ እስረኞች ስቃይ ወይም ቶርቸር ግምገማ ኮሎምቢያ የመጀመሪያዋ ተገምጋሚ ሀገር ስትሆን ኢትዮጵያ ደግሞ የመጨረሻዋ ሀገር መሆኗን የግምገማ መርሀ ግብሩ ያስረዳል።

ኢትዮጵያ ተመድ የእስረኞችን እና ሌሎች በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎችን ስቃይ ወይም ቶርቸር ለመከላከል የተዘጋጀውን ስምምነት የተቀበለች ሲሆን የስምምነቱ አተገባበር ከሚያዝያ ከ25 እስከ 26 ቀን 2015 ዓ. ም በጀኔቫ ይገመገማል።

ይህን ስምምነት 173 የዓለማችን ሀገራት የፈረሙ ሲሆን ተመድ በየጊዤው የፈራሚ ሀገራትን አፈጻጸም ይከታተላል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *