በአጣዬ ዙሪያ ዳግም ጦርነት ተነሳ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሚያ ብሄረሰብ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢዎች ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ጦርነት መጀመሩን የአይን እማኞች ለኢትዮ ነጋሪ ገልጸዋል፡፡

በኦሮሞ በሄረሰብ ዞን ስር ካሉ ወረዳዎች መካከል አንዱ ከሆነው ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ሰንበቴ ከተማ የተነሱ ታጣቂዎች ወደ ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ስራ ካለችው አላላ ቀበሌ በመሄድ የሰብል ስብሰባ ላይ የነበሩ አርሶ አደሮች ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ነዋሪዎቹ አክለዋል፡፡

ተኩሱን ተከትሎም ወደ አካባቢው ባሉ ሌሎች ቀበሌዎች ጦርነት የተጀመረ ሲሆን ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን ጥለው ተሰደዋል ተብሏል፡፡

በአካባቢው የነበረው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጦርነቱን ለማስቆም ሞክሮ እንዳልተሳ የነገሩን ነዋሪዎቹ ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ተጨማሪ ሀይል ከአጎራባች አካባቢዎች በመግባት ላይ ነውም ብለውናል፡፡

ከሁለት ወር በፊት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ሰንበቴ እና ጀውሃ ከተሞች የነበሩ የልዩ ሀይል አባላትን በመግደል የጦር መሳሪያዎችን መዝረፋቸው ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ወደ ስፍራው የገባው የፌደራል ጸጥታ ሀይል ዝረፍያውን በፈጸሙ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ እንዳልወሰደ የነገሩን ነዋሪዎቹ አሁን በነዋሪዎች ላይ ከባድ ጥቃት የከፈቱት በዚህ የጦር መሳሪያ መሆኑንም አክለዋል፡፡

አጣዩ ከተማ እና አካባቢው በተደጋጋሚ ከኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ስራ ባሉ ወረዳዎች በሚነሱ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት ያደረሱ ሲሆን በታጣቂዎቹ ላይ እርምጃ አለመወሰዱ ጥቃቱ አሁንም እንዲቀጥል ማድረጉ ተገልጿል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *