የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በታጣቂዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ።

የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ ዛሬ ጠዋት በመኖሪያ ቤታቸው በር ላይ መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች መገደላቸውን የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል።

ኃላፊው ወደ ስራ ለመሄድ ከቤታቸው በወጡበት ጊዜ በተተኮሰባቸው ጥይት እንደተገደሉም ነው የከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት በማህበራዊ ገጽ ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው።

አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ከመሾማቸው አስቀድሞ የነቀምቴ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊነትን ጨም በተለያዩ ስፍራዎች ላይ ሲያገለግሉ መቆየታቸውም ተገልጿል።

የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ መገደልን ተከትሎ የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማም የተሰማቸውን ሀዘን መግለጻቸወን ፓርቲው አስታውቋል።

አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ ከህዝብ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት በጠዋት ወደ ስራ ገበታቸው በመሄድ ላይ እያሉ በጨካኞች በተፈፀመባቸው ግድያ ማዘናቸውንም የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ኃላፊ ገልጸዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *