መንግሥት በህወሀት አመራሮች ላይ የመሰረተውን ክስ አቋረጠ።
የፍትህ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ በፌዴራል መንግስት እና በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) መሃከል በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት ከግጭቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወንጀሎች ተጠያቂነት በተመለከተ ያለውን ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ ሊታዩ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብላል።
በመሆኑም በወንጀል ተጠርጥረዉ ክስ ቀርቦባቸዉ የነበሩ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮችን ክስ ማቋረጡን ሚንስቴሩ አስታውቃል።
ክሱ የተቋረጠላቸው ተከሳሾች ጉዳያቸዉ በቀጣይ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ እንደሚታይም ተገልጿል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ቀርቦ በክርክር ሂደት ላይ ይገኙ የነበሩ የወንጀል ክሶች በአዋጅ 943/2008 አንቀጽ 6 (3) (ሠ) መሰረት መነሳታቸውን ሚንስቴሩ ገልጻል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በህወሀት ላይ አጽድቆት የነበረውን የሽብርተነት መዝገብ ባሳለፍነው ሳምንት ማንሳቱ ይታወሳል።