በአዲስ አበባ የቡና አፈላል አውደ ርዕይ ሊዘጋጅ እንደሆነ ተገለጸ

በአዲስ አበባ የቡና አፈላል አውደ ርዕይ ሊዘጋጅ እንደሆነ ተገለጸ

የኢትዮጵያዊያን ባህል ለማስተዋወቅ ዋና ዓላማው ያደረገ የኢትዮጵያ ቡቡና አፈላል ሂደትን እና ተያያዥ ባህልን የሚያሳይ አውደ ርዕይ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል።

በዋርካ ኮፊ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት አማካኝነት የተዘጋጀው ይህ አውደ ርዕይ የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ይዘጋጃል ተብሏል።

የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሰዓዳ ሙስጠፋ በአውደ ርዕዩ ዝግጅት ዙሪያ በሰጡት መግለጫ “በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያ ቡና አቆላል፣ አጠጣጥ እና ተያያዥ ባህሎች ለታዳሚያን ይቀርባል” ብልዋል።

በዝግጅቱ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ መጋበዙን የሚናገሩት ወይዘሮ ሰዓዳ የኢትዮጵያን ቡና በመግዛት የሚታወቁ ሀገራት አምባሳደሮች እና ሌሎችም በእንግድነት እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

ከአዲስ አበባ ባህልና ኪነ ጥበባት ቢሮ ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው ይህ የቡና ባህል አውደ ርዕይ ኢትዮጵያዊያን ቡና ሲጠጡ የሚታወቁበት የንግግር ባህል፣ ግጭት አፈታት እና ሌሎች ዝግጅቶችም ለጎብኝዎች ይቀርባል ተብሏል፡፡

ይህ የኢትዮጵያ ቡና ባህል አውደ ርዕይ ከቀኑ 6-11 ሰዓት ውስጥ ለተመልካቾች ክፍት እንደሚሆን አዘጋጆቹ ጠቅሰዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *