መንግሥት ለአዲስ አበባ አመራሮቹ ለሞባይል ስልክ 140 ሺህ ብር ፈቀደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአመራሮች የእጅ ስልክ መግዣ 140 ሺህ ብር ድረስ ፈቀደ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በጥር ወር ላይ በወሰነዉ ዉሳኔ መሰረት፣ ለከተማዋ አመራሮች የሞባይል ስልክ ቀፎ ግዢ መፍቀዱ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ለከንቲባ እና ለከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ 140 ሺህ ብር ተመድቧል።

ለምክትል ከንቲባ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ደረጃ ለተሿሙ አመራሮች እና ለምክትል አፈ-ጉባኤ ስልክ መግዣ 120 ሺህ ብር መወሰኑንም ሰምተናል ሲል ኢትዮ ኤፍ ዘግባል።

ለክፍለ ከተማ 50 ሺህ ፣ለወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ የ40 ሺህ እንዲሁም ለወረዳ ቀሪ አመራሮች 30 ሺህ ብር የሚያወጣ የሞባይል ስልክ እንዲገዛላቸዉ ተፈቅዷል።

ይህንን የሚያስፈፅም ደብዳቤም በየክፍለ ከተማዎችና ወረዳዎች ጭምር እንደተበተነ ተገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *