ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመቋረጧ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተገለጸ

በሳሙኤል አባተ

ኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተገልጻል።

ቶፕ 10 ቪፒኤን የቴክኖሎጂ ኩባንያ እንዳስታወቀው፣ በትግራይ ክልል የነበረውን ጦርነት ተከትሎ ለአንድ አመት ሙሉ የኢንተርኔት አገልግሎት በመዘጋቱ ሃገሪቱ 146 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን አስታውቋል።

አሁንም ቢሆንም በመላው ሀገሪቱ ኢንተርኔት በመቋረጡ ሚሊዮን ዶላሮችን እያጣች ትገኛለች ብሏል።

ኢንተርኔት ከተዘጋ አንድ ወር ያለፈ ሲሆን መንግሥት እስካሁን ስለጉዳዩ ያለው ነገር የለም።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሚዲያ ምክር ቤት እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የኢትዮጵያ መንግሥት ኢንተርኔት እንዲከፍት ጠይቀዋል።

በአሁኑ ወቅት የኢንተርኔት ገደብ የተደረገባቸው ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ እና ዩቲዩብ  ገደብ የተደረገባቸው የትስስር ገጾች ናቸው።

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊትም የኢንተርኔት ገደብ በመጣል የምትታወቅ ሲሆን በተለይም የፖለቲካ አለመረጋጋት ሲፈጠር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ከማወጅ ጀምሮ ኢንተርኔትን ሙሉ ለሙሉ ሲዘጋ ቆይቷል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *