በኢትዮጵያ 22 ሚሊዮን ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ እንደማያገኙ ተገለጸ

በኢትዮጵያ 22 ሚሊዮን ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ እንደማያገኙ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ባለፉት ጊዜያት የተከሰቱ ሰው ሰራሽ የተፈጥሮ ችግሮች የተነሳ ቁጥራቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ዜጎች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በሚነሱ ችግሮች በከፍተኛ ሁኔታ ሰላባ የሚሆኔት ሴቶች መሆናቸውን ጥናቶች ያመላክታሉ።ይህንኑ ተከትሎ በኢትዮጵያ የወር አበባ ከሚያዩ ከ35 ሚሊዮን በላይ ሴቶች ውስጥ 22 ሚሊዮን ያህሉ የወር አበባ ንጽሕና መጠበቂያ እንደማያገኙ የአደይ የሚታጠብ ንጽሕና መጠበቂያ መሥራች ወይዘሮ ሚካል ማሞ ተናግረዋል።

22 ሚሊዮን ያህሉ ምንም አይነት ስለ ንጽህና መጠበቂያ መረጃ የማያገኙ መሆናቸውን የሚያስረዱት ሚካል ይህዉ ቁጥር በቀጣይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ስጋታቸዉን ገልጸዋል።ይህንን አስመልክቶ የአደይ የሚታጠብ ንጽሕና መጠበቂያ ድርጅት ዘላቂ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን በማምረት ላይ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

አንዲት ሴት በወር አበባ ምክንያት በአማካኝ ከሦስት እስከ አምስት ቀናት ከትምህርት ወይን ከሥራዋ በንጽሕና አቅርቦት እጥረት ምክንያት የምትስተጓጎል በመሆኑ ይህ ምርት በአማካይ ለ 2 አመት ያህል የሚያገለግል ከመሆኑ ባሻገር በስነልቦና ረገድ ጥቅሙ የጎላ ሴት ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ የመራቅ እድልን የሚያስቀር ነዉ፡፡

የአደይ የሴቶች የሚታጠብ ንጽሕና መጠበቂያ – ፓድ ምርት በኢትዮጵያ ያለውን የሴቶች የወር አበባ የንጽሕና መጠበቂያ አቅርቦት እጥረት ለመፍታት ይረዳል የተባለ ሲሆን በምርቶቹ ላይ የሚታዉን የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ያግዛል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

የትኛዋም ሴት የንጽሕና መጠበቂያ በማጣት ምክንያት ከትምህርት ገበታዋ ይሁን ከአስፈላጊ ሥራዎቿ መቅረት የለባትም የሚሉት ወይዘሮ ሚካል እስካሁንም በሀገሪቱ ለሚገኙ ከ300 ሺ በላይ ሴት ተማሪዎች የንጽሕና መጠበቂያ በመሥራት ተደራሽ ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል።

አደይ ፓድ የንጽሕና መጠበቂያ የሚታጠብ ሆኖ በአንድ የወር አበባ ኡደት ሁለት ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውል በአጠቃላይ አንድ መቶ ጊዜ መታጠብ የሚችል ነዉ።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *