ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ የ2023 ‹‹የዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት›› አሸነፈች

ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ የ2023 ‹‹የዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት›› አሸነፈች

መምህርት፣ ጋዜጠኛና አክቲቪስት መዓዛ መሐመድ የ2023 የ‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት (International Women of Courage/IWOC Awards)›› አሸናፊ ሆናለች፡፡ 

‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት›› በመላው ዓለም ከባድ አደጋዎችንና ፈተናዎችን ተቋቁመው ሰላም፣ ፍትህ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ የፆታ እኩልነት እና የሴቶች ተጠቃሚነት እንዲከበሩና እንዲሰፍኑ ልዩ ጥንካሬ፣ ጀግንነትና የአመራር ጥበብ ላሳዩ ሴቶች የሚበረከት ሽልማት ነው፡፡

ሽልማቱ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

እስካሁን ድረስም ከ80 ሀገራት የተገኙ ከ180 በላይ ጀግና ሴቶችን እውቅና ሰጥቷል፡፡

በዘንድሮው ሽልማት ከአራት አህጉራት የተገኙ 11 ጀግና ሴቶች እና አንድ የሴቶች ቡድን እውቅና ይሰጣቸዋል፡፡   

ለሽልማቱ የሚመረጡት ሴቶች የሚታጩት በየሀገራቱ በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች ሲሆን፤ የመጨረሻዎቹ አሸናፊዎች የሚመረጡት ደግሞ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናትና ባለሙያዎች ነው፡፡

የሽልማቱ አሸናፊዎች “International Visitor Leadership Program (IVLP)” በተባለው መርሃ ግብር በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በመዘዋወር ከሴቶች አደረጃጀቶች አመራሮች ጋር ይወያያሉ፤የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

ከ2023 የ‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት (International Women of Courage/IWOC Awards)›› አሸናፊዎች መካከልም አፍጋኒስታዊያኗ ዶ/ር ዘካሪያ ሒክመት ፣ አልባ ሩዳ ከአርጀንቲና፣ ፕ/ር ዳንኤላ ዳርላን – ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ዶሪስ ሪዮስ ከኮስታ ሪካ፣ መዓዛ መሐመድ ከኢትዮጵያ ዋነኞቹ ናቸው።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *